ጅማ አባ ጅፋር የሁለት ወር ደሞዝ ከፈለ

በአዲስ አደረጃጀት በቀጣይ ዓመት የተሻለ ቡድን ይዞ ለመቅረብ ጥረት እያደረገ የሚገኘው ጅማ አባ ጅፋር የሁለት ወር የተጫዋቾች ደሞዝ ከፈለ።

የ2012 የውድድር ዘመን ለተጫዋቾች ያልተከፈለ የሰባት ወር የደሞዝ ዕዳ ያለበት ብቸኛ ክለብ የሆነው ጅማ አባጅፋር አዲስ የክለቡ የበላይ ጠባቂ ካገኘ ወዲህ የተሻሉ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል። ለዚህ ማሳያ እንዲሆን ዛሬ የሁለት ወር የተጫዋቾች ደሞዝ መክፈሉን ሰምተናል።

ቀሪ የአምስት ወር ደሞዝ ከፍሎ ያላጠናቀቀ ቢሆንም በቀጣይ ጊዚያት ክፍያውን ለማጠናቀቅ እንዳቀደ ለማወቅ ችለናል። ክለቡን በበላይነት የሚመሩት የጅማ ከተማ አዲሱ ከንቲባ አቶ ቲጃኒ ናስር በክለቡ ውስጥ ያለው የአስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ እና ክለቡ ትክክለኛ አደረጃጀት እንዲኖረው በማድረግ ህዝባዊ ክለብ ሆኖ እንዲቀጥል ለማድረግ በቀጣይ ሌሎች ውሳኔዎችን ይወስናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!