ትውልደ ኢትዮጵያዊው አማካይ ወደ ሊቨርፑል?

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ታዳጊ መልካሙ ፍራውንዶርፍ ወደ ሊቨርፑል የሚያደርገው ዝውውር ስለ መጠናቀቁ ፍንጭ ሰጥቷል።

በኢትዮጵያ ከምባታ ጠምባሮ ዞን ተወልዶ የእግርኳስ ሕይወቱን በጀርመኑ ክለብ በሆፈንሄም የጀመረው የ16 ዓመቱ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የአጥቂ አማካይ በጀርመን ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው ታዳጊዎች አንዱ ሲሆን ሊቨርፑልም የግሉ ለማድረግ ለወራት ሲከታተለው እንደቆየ ተገልጿል። ተጫዋቹ በኢንስታግራም ገፁ ፕሮፋይል ላይ የሊቨርፑልን ስም ማስፈሩን ተከትሎም በርካታ የእግሊዝ ሚድያዎች ወደ ሊቨርፑል የሚያደርገውን ዝውውር ስለማጠናቀቁ እየዘገቡ ይገኛሉ።

በሁለት የዕድሜ እርከኖች የጀርመንን ብሔራዊ ቡድን በአምበልነት የመራው መልካሙ ወደ ሊቨርፑል የሚያደርገውን ዝውውር ካጠናቀቀ የክለቡን ወጣት ቡድን እንደሚቀላቀል ሲጠበቅ ታላቅ ወንድሙ መለሰ ፍራዮንዶርፍን ጥሎ ወደ መርሲሳይድ የሚያመራም ይሆናል።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ