የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ የሚደረግበት ቀን ታውቋል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዓመታዊው ጠቅላላ ጉባዔ ቀን እና ቦታ ታውቋል።

በመስከረም 2013 ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ጉባዔው መንግስት ባወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት ቀኑ ላልታወቀ ጊዜ መራዘሙን ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል፡። ሆኖም ስፖርቶች ወደ ውድድር በመመለሳቸው እና ተጥሎ የነበሩ ገደቦች በመነሳታቸው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቀደም ብሎ አራዝሞት የነበረውን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔን ኅዳር 26 በሀዋሳ ከተማ እንዲደረግ በደብዳቤ ገልፆ ለአባላቱ ልኳል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ


👉ሳንዘናጋ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!