Soccer Ethiopia

Archives

​ሶከር ሜዲካል | የአዕምሮ መዛል በእግር ኳስ [ክፍል 2]

ከዚህ በፊት በነበረው የሶከር ሜዲካል ፅሁፋችን በእግር ኳስ ተጫዋቾች የአዕምሮ መዛል መንስኤዎች መካከል የሆነውን መዋቅራዊ ተፅዕኖ ተመልክተናል። በዚህኛው ፅሁፍ ደግሞ ከስነ ልባና ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ጫናዎችን እንመለከታለን። አትሌቲክ በተሰኘው የእግር ኳስ ድረ ገፅ የሰፈረውን ” we need to talk about mental burnout in football.” እንደ ግብዐት ተጠቅመናል።  ሥነ ልቦናዊ ጫናዎች በሚኖሩበት ጊዜ ተጫዋቾች በፍጥነት ከጉዳት […]

ሶከር ሜዲካል| የአዕምሮ መዛል በእግርኳስ [ክፍል 1]

በዚህ ሳምንት አምዳችን በእግር ኳስ ከሚያጋጥሙ ችግሮች መካከል አንዱ ስለሆነው ነገር ግን የሚገባውን ትኩረት ስላላገኘው የአዕምሮ መዛል (mental burnout ) እንመለከታለን። በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የእግር ኳስ ውድድሮች በመካሄድ ላይ ይገኛሉ። ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው የሀገራችን የክለቦች ውድድር ለመመለስ የተቃረበ ሲሆን ብሄራዊ ቡድናችንም በ3 የወዳጅነት ጨዋታዎች ወደ እግር ኳሱ ተመልሷል። በቅርብ ቀናትም ኒጀርን የሚገጥም ይሆናል። እግር […]

ሶከር ሜዲካል | እግር ኳሳችን እና ህክምና …

ከእግርኳስ ጋር የተገናኙ የህክምና መረጃዎችን ወደ እናንተ በምናደርስበት የሶከር ሜዲካል ዓምዳችን በቅርቡ ወደ ልምምድ ወደተመለሰው እና ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ወዳደረገው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትኩረታችንን ለማዞር ወደድን። በዚህ ጉዳይ ላይ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የህክምና አባል የሆነችው ዶክተር ቃልኪዳን ዘገየን አናግረናል። ከቆይታችን ብዙ እንደምትማሩ ተስፋ እናደርጋለን። ዶክተር ቃልኪዳን በፈቃደኝነት ለሰጠችን መልስ እና ስለ ትብብሯ በእናንተ ክቡር […]

ሶከር ሜዲካል | የደጋፊዎች ወደ ስታዲየም መመለስ እና የጤና ጉዳይ

የCovid-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ በኋላ ብዙ የሚባሉ የሕይወታችን አካላት ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል። እግርኳስም በዚህ ተፅዕኖ ሥር ከወደቁ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው። ምንም እንኳ በአውሮፓ የሚገኙ ታላላቅ ውድድሮች ከጥቂት ወራት ቆይታ በኋላ ቢመለሱም በሀገራችንም ሆነ በአፍሪካ አብዛኛው ቦታዎች እግር ኳስ ውድድሮች እየተካሄዱ አይደለም። ሀገራት ውድድሮችን ተመልካቾች በማይገኙበት ሁኔታ በዝግ ስቴዲየም ሲያካሂዱ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው። በቅርቡ ውድድሮችን ለመመለስ […]

ሶከር ሜዲካል | ስብራት እና ውልቃት

በእግር ኳስ በጣም ተዘውትረው ከሚታዩ ህመሞች ወይንም ጉዳቶች የአጥንት መሰመር እና የመገጣጠሚያ አካባቢ የሚኖር መውለቅ አደጋዎች የሚጠቀሱ ናቸው። ከአጠቃላይ ጉዳቶችም 10% የሚሆነውን ድርሻ ይይዛሉ። በእግር ላይ የሚያጋጥሙ ስብራቶች 44.4% ድርሻውን የሚይዙ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ በእጅ ላይ የሚደርሱት ወደ 27% የሚጠጉት ናቸው። በዚህ ሳምንት የሶከር ሜዲካል ዓምዳችን የምንመለከተውም የስብራት እና ውልቃት መንስኤ እና መገለጫዋች እንደዚሁም እንዴት […]

ሶከር ሜዲካል | ፊት ላይ የሚደርሱ ስብራቶች

አገጭ ፣ ጉንጭ ፣ ጥርስ እና የመሳሰሉት የፊት አካላት በግጭት ወቅት ጉዳት የሚደርስባቸው አካላታችን ናቸው። በዛሬው ዐምዳችን የምንመለከተው የፊት አጥንቶች ሲሰበሩ የሚደርሱ ጉዳቶችን ነው።   Mandibular Fracture (የአግጭ ስብራት) የዚህ ስብራት መገለጫዋች ህመም ፣ ማበጥ ፣ መገጣጠሚያን ለማንቀሳቀስ መቸገር ፣ ለማላመጥ መቸገር፣ የአይን ጉዳት እና የጥርስ ስብራት ናቸው። በህክምና ወቅት ተያያዥነት ያላቸው ከፍተኛ ጉዳቶች ማለትም […]

ሶከር ሜዲካል | ፊት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች

በተደጋጋሚ እንደሚነገረው እግር ኳስ የንክኪ ስፖርት ነው። ተጫዋቾች እርስ በእርሳቸው ከሚያደርጉት ንክኪ በተጨማሪ ከመሬት፣ ከኳስ እና በግብ ጠባቂዎች ምሳሌ ደግሞ ከግቡ ቋሚ ጋር ሊጋጩ የሚችሉበት ዕድል ከፍ ያለ ነው። ማንኛውም ፊት ላይ የሚደርስ ጉዳት ከፍተኛ ችግር የማስከተል ዕድሉ ላቅ ያለ ስለሆነ በጥንቃቄ ሊመረመር እና ሊታከም ይገባል። በአብዛኛው ጊዜ የጭንቅላት ግጭት እና ክርን ከጭንቅላት ጋር የሚኖረው […]

ሶከር ሜዲካል | የደረት ጉዳት በእግር ኳስ

በእግርኳስ የደረት አካባቢ ጉዳቶች ተብለው የሚጠቃለሉት የደረት ጡንቻዎች ጉዳት እና የጎድን አጥንቶች ስብራት ናቸው። የጎድን አጥንቶች ሊሰበሩ ከሚችሉባቸው መንገዶች መካከል በእንቅስቃሴ ወቅት ከጠንካራ ነገር ጋር የሚኖር ግጭት በዋናነት የሚገለፅ ነው። እንደምሳሌ ለመውሰድ ተጫዋቹ በደረቱ አካባቢ በክርን ቢመታ ይህ ጉዳት ሊያጋጥመው ይችላል። ከዚህ በተጨማሪም በሀይል መሬት ላይ መውደቅ እና ከግብ ቋሚ ጋር መላተም ተመሳሳይ አይነት ጉዳቶች […]

ሶከር ሜዲካል | ሆድ ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች

በእግር ኳስ ውስጥ በሆድ አካባቢ የሚደርሱ ጉዳቶች በተደጋጋሚ የሚከሰቱ ባይሆኑም በቅርብ ዓመታት በቁጥር እየጨመሩ መጥተዋል። የተለመደ ጉዳት ካለመሆኑ የተነሳ በቶሎ ላይታወቅ እና ላይታከም የሚችልበት ዕድልም ሰፋ ያለ ነው። ከዚህም በተጨማሪ እንደ አጥንትና ጡንቻ ላይ እንደሚደርሱ ጉዳቶች ግልፅ ምልክት ላይኖረው ይችላል ። የዚህም ምክንያት በሆድ ውስጥ የሚገኙ የሰውነት አካላት ( intra-abdominal organs) ሲጎዱ ወዲያውኑ በቀላሉ ለመለየት […]

ሶከር ሜዲካል | የአንጎል ጉዳት በእግርኳስ

ከእግር ኳስ የተያያዙ የህክምና ጉዳዮችን በምንዳስስበት የሶከር ሜዲካል ዓምዳችን የዛሬ ፅሁፍ ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባውን እና እንደ እግርኳስ ባሉ የንክኪ ስፖርቶች በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የአንጎል ጉዳት የምንመለከት ሲሆን ጉዳቱ ካጋጠመ በኋላ ተጫዋቾች በጥሩ ሁኔታ እንዲያገግሙ መደረግ የሚኖርባቸውን እርምጃዎች የምንመለከት ይሆናል። እግር ኳስ በከፍተኛ ፍጥነት የሚከወን የንክኪ ስፖርት እንደመሆኑ በሜዳ ላይ ግጭቶች የተለመዱ ናቸው። ጭንቅላት ላይ የሚደርሱ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top