Soccer Ethiopia

Archives

ጥቂት ነጥቦች በብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ምርጫ ዙርያ..

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታውን እያከናወነ ይገኛል። ከ15 ቀናት በኋላም የምድቡን ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች በተከታታይ ከኒጀር ጋር ከሜዳው ውጪ እና በሜዳው ሲያከናውን ለዚህ ዝግጅት ይረዳው ዘንድ ለ24 ተጫዋቾች በትናንትናው ዕለት ጥሪ አድርጓል። ምርጫውን ተመርኩዘንም ጥቂት ነጥቦችን በሚከተለው መልኩ ለማንሳት ሞክረናል። እነማን ተመረጡ? ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለሚከናወኑት ጨዋታዎች ከተመረጡት 24 ተጫዋቾች መካከል […]

የፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ዓበይት ጉዳዮች (፬) – ሌሎች ጉዳዮች

የሳምንቱ ዓበይት ጉዳዮች ቅኝታችንን ቀጥለን ሌሎች ሊነሱ የሚገባቸው የሳምንቱ ጉዳዮችን እንዲህ ተመልክተኛቸዋል። 👉ዳኞቻችን እና የአዲሱ የጨዋታ ህግ ትውውቅ የዓለምአቀፉ የእግርኳስ ማኅበራት ቦርድ (IFAB) የእግርኳስ ጨዋታ የሚመራባቸው ህግጋትን የመከለስና የማሻሻያ ስራዎች በተለያዩ ጊዜያት ሲከውን ይስተዋላል። በዚህም መሠረት ባሳለፍነው የፈረንጆች አቆጣጠር ጁን አንድ ጀምሮ በተወሰኑ የጨዋታ ህጎች ላይ ማሻሻያ ማድረጉ ይታወሳል። ከአስራ ሰባቱ የጨዋታ ህጎች ላይ ወደ […]

የፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ዓበይት ጉዳዮች (፫) – አሰልጣኞች ትኩረት

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ ከአሰልጣኞች ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እና ዐበይት አስተያየቶችን እንዲህ አጠናቅረናቸዋል። 👉 ሲሳይ አብርሃም እና ከፊቱ የተደቀነው ፈተና ከቀናት በፊት ከአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር የተለያዩት ስሐል ሽረዎች ባሳለፍነው ዓርብ አሰልጣኝ ሲሳይ አብርሃምን በዋና አሰልጣኝነት መቅጠራቸው ይታወሳል። ከአዲሱ ሹመታቸው ማግስት ቡድኑ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በኢትዮጵያ ቡና አሰቃቂ የሆነ […]

የፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ዓበይት ጉዳዮች (፪) – ተጫዋች ትኩረት

የሳምንቱን ዐበይት ጉዳዮች የምንመለከትበት ሁለተኛው ክፍል ትኩረት የሳቡ ተጫዋች ነክ ክስተቶችን ይመለከታል። 👉 ከጨዋታ ርቀው የከረሙ ተጫዋቾች በጥሩ ብቃት ዳግም መመለስ በአጋማሹ የዝውውር መስኮት ከአንድ ዓመት እስከ ግማሽ የውድድር ዓመት ድረስ ያለክለብ የቆዩ እንዲሁም በነበሩባቸው ክለቦች የመሰለፍ እድል ጨርሶውኑ ያላገኙ ተጫዋቾች ወደ ተለያዩ ክለቦች ያመሩባቸውን ዝውውሮችን እየፈፀሙ ይገኛል። ለአብነትም አልሀሰን ካሉሻ፣ ተስፋዬ በቀለ፣ ዮናስ በርታ፣ […]

የፕሪምየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ዓበይት ጉዳዮች (፩) – ክለብ ትኩረት

ሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከአስራ አምስት ቀናት እረፍት በኋላ በዚህኛው ሳምንት ሲመለስ የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያልተጠበቀ ሽንፈት በማስተናገድ ደረጃውን አዳማን ለረታው ፋሲል ለማስረከብ ተገዷል። መቐለ ከሜዳው ውጪ ወሳኝ ድል ሲያስመዘግብ ሲዳማም ተከታታይ አራተኛ ድሉን አሳክቷል። ኢትዮጵያ ቡና በሳምንቱ ከፍተኛ ግብ በማስቆጠረ ያሸነፈ ቡድን ሲሆን ድሬዳዋ ከተማም ከወራጅ ቀጠናው ማምለጡን ቀጥሎበታል። እኛም እንደተለመደው በዚህኛው […]

የአሰልጣኞች አስተያየት | ቅዱስ ጊዮርጊስ 0-1 ወልቂጤ ከተማ

በ16ኛ ሳምንት ሁለተኛ የጨዋታ ቀን ቅዱስ ጊዮርጊስ በሜዳው በወልቂጤ ከተማ 1-0 ከረታበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኃላ የሁለቱ ቡድኖች አሰልጣኞች ተከታዩን አስተያየት ሰጥተዋል።   “ተጫዋቾቼ ያሰበነውን እቅድ ለመተግበር ባሳዩት ጥረት የሚገባንን ውጤት አግኝተናል” ደግአረግ ይግዛው (ወልቂጤ ከተማ) ስለጨዋታው ” ከሜዳችን ውጭ ያደረግነው እንደመሆኑ ጠንካራ ጨዋታ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ ትልቅ ታሪክ ያለውና በጠንካራ ተጫዋቾች የተገነባ ስብስብ ነው። የኛ […]

ሪፖርት | ወልቂጤዎች አስደናቂ ድልን በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ተቀዳጁ

በ16ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ የጨዋታ ቀን አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ወልቂጤን ያስተናገዱት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ያልተጠበቀ የ1-0 ሽንፈትን አስተናግደው መሪነታቸውን ለፋሲል ከተማ አስረክበዋል። የመጀመሪያውን ዙር በበላይነት ያጠናቀቁት ፈረሰኞቹ ከአዳማ ከተማ ጋር በ15ኛ ሳምንት አቻ ከተለያየው የቡድን ስብስብ ውስጥ የሶስት ተጫዋቾች ለውጦችን ሲያደርጉ በዚህም ሰልሀዲን በርጌቾ ፣ የአብስራ ተስፋዬ እና ጋዲሳ መብራቴን በአሰላለፍ ውስጥ አስገብተዋል። […]

የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ቡና 6-1 ስሁል ሽረ

በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ የጨዋታ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡና አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ስሑል ሽረን አስተናግዶ 6-1 ካሸነፈበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል። “ጨዋታው ከውጤት አንፃር ጥሩ ነው” ካሳዬ አራጌ (ኢትዮጵያ ቡና) ስለ ጨዋታው ” ጨዋታው ከውጤት አንፃር ጥሩ ነው ፤ ብዙ ጎሎችን ማስቆጠር ችለናል። ነገር ግን በቀላሉ አንዳንድ እንቅስቃሴው ሊቀጥልባቸው […]

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 1ኛ ዙር ክለቦች ዳሰሳ – ሲዳማ ቡና

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አንደኛውን ዙር ዳሰሳ የምንዘጋው በመጨረሻዎቹ ሳምንታት መሻሻል በማሳየት በ24 ነጥቦች 4ኛ ደረጃ ይዞ ዙሩን ባጋመሰው ሲዳማ ቡና ይሆናል። የውድድር ዘመኑ ጉዞ በሊጉ በውጤትም ሆነ በስብስብ ደረጃ የተረጋጉ ከሚባሉት ክለቦች አንደኛው የሆነው ሲዳማ ቡና በክረምቱ ወሳኝ ተጫዋቾቹን በማቆየት እምብዛም ዝውውር ላይ ሳይሳተፍ መቐለ ላይ የተደረገውን የትግራይ ዋንጫ በማሸነፍ ነበር ወደ ውድድር የገባው። በመጀመርያው […]

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 1ኛ ዙር ክለቦች ዳሰሳ – ወላይታ ድቻ

በተከታዩ መሰናዷችን ከመጥፎ አጀማመር በኋላ ቀስ በቀስ ወደ ጥሩ አቋም በመምጣት በ21 ነጥቦች 7ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥ አጋማሹን ያጠናቀቀው ወላይታ ድቻን እንመለከታለን። የውድድር ዘመን ጉዞ ቡድኑን ለረጅም ዓመታት ከመሩት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ጋር ከተለያየ በኋላ በአሰልጣኝ ቅጥር ዙርያ መረጋጋት የተሳነው ወላይታ ድቻ ዓምና ዘነበ ፍስሀን በውጤት ማጣት የተነሳ የመጀመርያው ዙር መገባደጃ ላይ ከኃላፊነት ካነሳ በኋላ […]

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top