አማኑኤል ጎበና አዳማ ከተማን ለመቀላቀል ተስማማ

በትናንትናው ዕለት ከሁለት ተጫዋቾች ጋር የተስማሙት አዳማ ከተማዎች አማኑኤል ጎበናን ወደ ቡድናቸው ለመቀላቀል ተስማምተዋል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ታዳጊ ቡድን ተነስቶ በአርባምንጭ ከተማ ለበርካታ ዓመታት የተጫወተው አማካዩ በወልዋሎ የአንድ ዓመት ቆይታው ጥሩ ብቃት ያሳየ ሲሆን በተለይም በሁለተኛው ዙር ጉዳት እስካስተናገደበት ወቅት የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች መሆን ችሎ ነበር።

ተጫዋቹ ወልዋሎን የለቀቀ ሦስተኛ ተጫዋች ሲሆን ለአዳማ ከተማዎችም ሦስተኛ ቡድኑን ለመቀላቀል የተስማማ ተጫዋች ሆኗል። በርካታ የአማካይ ስፍራ ተጫዋቾችን በያዘው ቡድን ውስጥም ለተሰላፊነት ፉክክር ይጠብቀዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡