አቤል እንዳለ ለታዳጊዎች የትጥቅ ድጋፍ አደረገ

በቅርቡ ፈረሰኞቹን የተቀላቀለው አቤል እንዳለ ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ለሚገኙ ታዳጊዎች የትጥቅ ድጋፍ አድርጓል።
ወጣቱ አማካይ ባደገበት ሐረር ከተማ ለሚገኙ እድሜያቸው ከ13–16 ዓመት ለሚገኙ ለሁለት ወንድ ታዳጊ ቡድኖች እና ለአንድ የሴቶች ታዳጊ ቡድን ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የተለያዩ ትጥቆች፣ መጫወቻ ኳሶች እና የልምምድ መስርያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ያደረገው።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በቅድመ ውድድር ዝግጅት ቢሾፍቱ የሚገኘው አቤል በቅርብ ዓመታት በኢትዮጵያ እግርኳስ ጎልተው ከወጡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ሲሆን የእግርኳስ ህይወቱን መነሻ በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ አድርጎ በደደቢት ከተሳካ ቆይታ በኃላ በቅርቡ ፈረሰኞቹን መቀላቀሉ ይታወሳል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተለያዩ ሊጎች እየተጫወቱ የሚገኙ ተጫዋቾች እንደ አቤል ሁሉ ያደጉበትን አካባቢ ዞር ብሎ በማየት የሚያደርጉት በጎ ተግባራት ለሌሎችም መሰል ተጫዋቾች ትልቅ ምሳሌ የሚሆን ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ