ታፈሰ ሰርካ በቀጣይ ዓመት የመቐለን ማልያ የሚለብስ አምስተኛ አዲስ ተጫዋች ሆኗል

ከሌሎች ክለቦች ቀደም ብለው በዝውውሩ እየተሳተፉ የሚገኙት ምዓም አናብስት የመከላከያው የመስመር ተከላካይ ታፈሰ ሰርካ የግላቸው ለማድረግ ተስማምተዋል።

ከዚ በፊት በደቡብ ፖሊስ እና በመከላከያ መጫወት የቻለው ይህ ተጫዋች በሁለቱም የመከላከል መስመሮች መጫወት የሚችል ሲሆን በተለይ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት የአቼምፖንግ አሞስን ግልጋሎት ባላገኘውና በሥዩም ተስፋዬ ላይ ብቻ ጥገኛ ለነበረው ቦታ ጥሩ ተፎካካሪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

በተያያዘ በቀጣይ ወር ላላቸው የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ የትግራይ ስታዲየምን ለመጠቀም በጥረት ላይ የሚገኙት ምዓም አናብስት በትናንትናው ዕለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኩል ለካፍ ጥያቄ አቅርበዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡