ያሬድ ብርሃኑ ወደ መቐለ ተመልሷል

ከወልዲያ ጋር በስምምነት የተለያየው ያሬድ ብርሀኑ ማረፊያው መቐለ ከተማ ሆኗል

ያሬድ ብርሀኑ በ2007 መቐለ ከተማ በብሔራዊ ሊጉ ምድብ ሀ የበላይ ሆኖ ባጠናቀቀበት ወቅት ስኬታማ ዓመት አሳልፎ 2008 ላይ ደደቢትን ቢቀላቀልም በሰማያዊዎቹ ቤት እምብዛም የመሰለፍ እድል ማግኘት አልቻለም። ይህን ተከትሎም በቀጣዩ አመት የውድድር አጋማሽ ዝውውር መስኮት በውሰት ወልድያን ተቀላቅሎ መልካም ጊዜን በማሳለፍ በያዝነው አመት መጀመርያ በቋሚነት ለወልዲያ ፈርሞ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ከመጀመሪያው ዙር መገባደጃ ሳምንታት ጀምሮ ከክለቡ ጋር ገብቶበት በነበረው አለመግባባት መነሻነት የተጣለበትን ቅጣት ከፍሎ በስምምነት በመለያየት ወደ መቐለ ከተማ አምርቷል።

ያሬድ ዘንድሮ ሊጉን ለተቀላቀለው መቐለ ከተማ በዘንድሮው የውድድር ዓመት የፈረመ 18ኛው ተጨዋች ሆኗል።