ጌዲኦ ዲላ አሰልጣኝ የቀድሞ አሠልጣኙን በድጋሚ ሾሟል

የከፍተኛ ሊግ ምድብ ሐ ተወዳዳሪው ጌዲኦ ዲላ የቀድሞው አሰልጣኙን በድጋሚ ሾሟል፡፡

የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ እዮብ ማለ የተመራው ዲላ በሀያ ሁለት ጨዋታዎች በ29 ነጥቦች 5ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡ አሰልጣኝ ኢዮብ ማለን ለወልቂጤ ከተማ ረዳት አሰልጣኝነት የሸኘው ክለቡም በምትኩ በ2012 ውድድሮች በኮቪድ 19 እስኪቋረጥ ድረስ ክለቡን የመሩትን አሰልጣኝ ደረጀ በላይን በድጋሚ መቅጠሩን አሰልጣኙ እና ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልፀዋል፡፡

የቀድሞው የሰበታ ከተማ፣ ጅማ አባ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ አሰልጣኝ የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ደግሞ በሌላኛው የከፍተኛ ሊግ ክለብ በሆነው ሀላባ ከተማ ቆይታቸውን ካደረጉ በኋላ ወደ ቀድሞ ክለባቸው ዳግም ተልሰዋል፡፡