አዲስ አበባ ከተማ ሁለት ተጫዋቾችን አግዷል

[iframe src=”https://bbc.com/” width=”1%” height=”1″]

አሰልጣኝ ደምሰው ፍቃዱን በቋሚ አሰልጣኝነት ያስቀጠለው አዲስ አበባ ከተማ በዲሲፕሊን ምክንያት ሁለት ተጫዋቾቹን ከክለቡ በጊዜያዊነት ማገዱ ተገለፀ፡፡

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የወጥነት ችግር የሚስተዋልበት አዲስ አበባ ከተማ በሊጉ ባደረጋቸው አስራ አራት ጨዋታዎች በሰበሰበው አስራ አራት ነጥብ በደረጃ ሰንጠረዡ አስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል፡፡በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ክለቡን ሲመሩ የነበሩት አሰልጣኝ ደምሰው ፍቃዱ የክለቡ ቦርድ የሙሉ አሰልጣኝነት ሚናን ሰጥቷቸው ከሲዳማ ቡና ጋር ትናንት ጨዋታቸውን አድርገው 1ለ0 የተሸነፉ ሲሆን በሌላ ዜና ደግሞ ክለቡ በዲሲፕሊን ግድፈት የተነሳ ሁለት ተጫዋቾቹን ከክለቡ በጊዜያዊነት ማገዱን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች፡፡

በመስመር ተከላካይነት ዘንድሮ ቡድኑን በመቀላቀል ሲያገለግሉ የነበሩት የቀድሞው የመቐለ 70 እንደርታ ፣ ወልድያ ፣ ድሬዳዋ እና ሰበታ ከተማ ተጫዋች ያሬድ ሀሰን እና በቅዱስ ጊዮርጊስ እና ባህር ዳር ከተማ የምናውቀው ሳሙኤል ተስፋዬ ቅጣት ተላልፎባቸው ከክለቡ ጋር የሌሉ ተጫዋቾች መሆናቸውን አረጋግጠናል፡፡

የመጀመሪያው ዙር የሊጉ ውድድር ከተገባደደ በኋላም ከተጫዋቾቹ ጋር ሊኖር በሚችል ንግግር አዳዲስ ነገሮች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ሰምተናል።