[restabs alignment=”osc-tabs-center” responsive=”false” tabcolor=”#dd3333″ tabheadcolor=”#ffffff”]
[restab title=”ድምፅ መስጫ” active=”active”]

በወንዶች እግርኳሰ

[socialpoll id=”2385802″]

በሴቶች እግርኳስ

[socialpoll id=”2385807″] [/restab]
[restab title=”ስለ ሽልማቱ”]
ይህ ሽልማት በአንድ አመት ውስጥ በእግርኳሱ ተፅእኖ ለፈጠሩ ግለሰቦች የሚሰጥ ሽልማት ነው፡፡ ከሜዳ ውስጥ ውጤታማነት ባሻገር በአጠቃላይ እግርኳሱ ላይ የሚገኙ ማናቸውም ግለሰቦች በዚህ ሽልማት ውስጥ ይካተታሉ፡፡

ከነዚህም መካከል
ተጫዋቾች ፣ አሰልጣኞች ፣ ዳኞች ፣ የህከምና ባለሙያዎች ፣ የአስተዳደር ሰዎች ፣ የሚድያ ባለሙያዎች ፣ ደጋፊዎች ፣ በጎ ፍቃደኞች እና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡

በሜዳ ላይ ድንቅ አቋም የሳየ ተጫዋች ፣ ውጤታማ አመት ያሳለፉ አሰልጣኞች እና ባለሙያዎች ፣ እግርኳሱን አንድ ደረጃ ከፍ ለማድረግ አስተዋጽኦ ያደረጉ ፣ ከዚህ ቀደም ያልታየ አዲስ ነገር ያሳዩ ወይም ግኝት ያገኙ ፣ ለችግሮች መፍትሄ የሰጡ እና የመሳሰሉት ለሽልማቱ እንደ መስፈርትነት ያገለግላሉ፡፡

የውድድሮች ደረጃ እና የሀገሪቱ የእግርኳስ እርከኖች ለሽልማቱ አንድ መስፈርት ናቸው፡፡

ዘርፍ

ይህ ሽልማት ባለፈው አመት ሲጀመር ዘርፉ አንድ የነበረ ሲሆን በሁለቱም ፆታ የሚገኙ ግለሰቦች አንድ ላይ ተወዳድረዋል፡፡ በዘንድሮው አመት ዘርፉ ወደ ሁለት ከፍ ብሎ በወንዶች እግርኳስ አና ሴቶች እግርኳስ በሚል ተከፍሏል፡፡

የወንዶች እግርኳስ

በዚህ ዘርፍ በወንዶች እግርኳስ ተፅእኖ የፈጠሩ ግለሰቦች ይሸለማሉ፡፡ በሁለቱም ጾታ ያሉ ግለሰቦች በወንዶች እግርኳስ ላይ እስካሉ ድረስ አሸናፊ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

-ለምሳሌ የወንድ ቡድንን የምትመራ ሴት አሰልጣኝ በዚህ ዘርፍ ትወዳደራለች፡፡

የሴቶች እግርኳስ

በዚህ ዘርፍ በሴቶች እግርኳስ ተፅእኖ የፈጠሩ ግለሰቦች ይሸለማሉ፡፡ በሁለቱም ጾታ ያሉ ግለሰቦች በሴቶች እግርኳስ ላይ እስካሉ ድረስ አሸናፊ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

-ለምሳሌ የሴቶች ቡድንን የሚመራ ወንድ አሰልጣኝ በዚህ ዘርፍ ይወዳደራል፡፡

ድምፅ አሰጣጥ
በዚህ ሽልማት 70% ድምጽ የሚሰጡት የሶከር ኢትዮጵያ ኤዲቶርያል አባላት ሲሆኑ የድረ ገፃችን አንባቢያን ድምፅ 30% ይይዛል፡፡

[/restab]
[restab title=”ስለ እጩዎቹ”]

ጌታነህ ከበደ

ብሄራዊ ቡድኑ በ2008 መልካም የሚባል የውድድር ዘመን ባያሳልፍም በግሉ ጎልቶ መውጣት ችሏል፡፡ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ በ6 ጨዋታዎች 6 ግቦችን ከመረብ ያሳረፈ ሲሆን በከፍተኛ ግብ አግቢነት ሰንጠረዡ የተቀደመው በአልጄሪያው አል አረብ ሱውዳኒ ብቻ ነው፡፡ አልጄርያ ላይ 3 ግቦች ማስቆጠር መቻሉም የጌታነህን ላቅ ያለ ደረጃ የሚያሳይ ነው፡፡
ጌታነህ ከአፍሪካ ዋንጫው በተጨማሪ በአለም ዋንጫ ማጣርያ ኮንጎ ላይ በደርሶ መልሱ 3 ግቦች ከመረብ አሳርፏል፡፡ በክለቡ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ፕሪቶርያ የተሰጠውን ጥቂት እድሎት በአግባቡ ተጠቅሞ ግቦችን አስቆጥሯል፡፡

ታፈሰ ተስፋዬ

ታፈሰ ተስፋዬ በእግርኳስ ህይወቱ ማምሻ ላይ ቢገኝም ግብ ከማስቆጠር ያገደው ነገር አልነበረም፡፡ የአዳማ ከተማው አጥቂ በ15 ግቦች የፕሪሚየር ሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን ለ5ኛ ጊዜ ያሸነፈ ሲሆን ለአዳማ መልካም የወድድር አመት ተጠቃሽ ተጫዋች ነበር፡፡

አስቻለው ታመነ

ባለፉት ሁለት አመታት እንደ አስቻለው ታመነ ወጥ አቋም ያሳየ ተጫዋች ማግኘት ያስቸግራል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ትልቁን ሚና የተጫወተ ሲሆን የፕሪሚየር ሊጉ ኮከብ ተጫዋች ለመሆንም በቅቷል፡፡ በብሄራዊ ቡድኑ የማጣርያ ጨዋታዎች እና የሴካፋ ውድድር ላይም ምርጥ ብቃቱን አሳይቷል፡፡

አብዱልከሪም መሃመድ

ታታሪው የመስመር ተከላካይ በቅርብ አመታት ከታዩ የመስመር ተከላካዮች ምርጡ የሚያሰኘው ድንቅ አቋም ላይ ይገኛል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና በሁለተኛው የውድድር ዘመን አጋማሽ ላሳየው መሻሻል ትልቁን ድርሻ የሚወስደውም አብዱልከሪም ነው፡፡

አሜ መሃመድ

አሜ በኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን እና በጅማ አባ ቡና ድንቅ አቋሙን አሳይቷል፡፡ የከፍተኛ ሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት በ21 ግቦች ሲያሸንፍ በ20 አመት በታች ቡድኑ ጋና እና ሶማልያ ላይ 3 ግቦች ከመረብ አሳርፏል፡፡


ሎዛ አበራ

በ2008 እንደ ሎዛ አበራ በእግርኳሳችን አስደናቂ አመት ያሳለፈ ግለሰብ አለ ለማለት ያስቸግራል፡፡ በብሄራዊ ቡድን ፣ በደደቢት እና በ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን ባደረገቻቸው 34 ጨዋታዎች 62 ግቦችን ማስቆጠር ችላለች፡፡ ከ20 አመት በታች ቡድኑን ለአለም ዋንጫ ለማሳለፍ ከጫፍ ስታደርስ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ከደደቢት ጋር አንስታለች፡፡

ፍሬው ኃይለገብርኤል

በመጀመርያ የውድድር ዘመኑ ደደቢትን ለፕሪሚየር ሊግ ድል አብቅቷል፡፡ ወጥ እና አሳማኝ ቡድን ይዞ የቀረበ ሲሆን ለተከታታይ አመታት በንግድ ባንክ ተይዞ የነበረውን ኃያልነት መገርሰስ ችሏል፡፡

አስራት አባተ

አሰልጣኝ አስራት የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድንን ለአለም ዋንጫ ለማሳለፍ ተቃርበው ነበር፡፡ የ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድኑ ተስፋ ሰጪ አቋም እንዲያሳይ የአስራት ሚና ከፍተኛ ነበር፡፡

ሊያ ሽብሩ

አንጋፋዋ ግብ ጠባቂ ወጥ የውድድር ዘመን በማሳለፍ ደደቢትን ለፕሪሚየር ሊግ ድል መምራት ችላለች፡፡ የሊጉ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆናም ተመርጣለች፡፡

እመቤት አዲሱ

ታዳጊዋ የመከላከያ አማካይ የወደፊቱ የኢትዮጵያ ሴቶች እግርኳስን እንደምትቆጣጠር ያሳየችበትን የውድድር ዘመን አሳልፋለች፡፡ በሁለት ክለቦች ተይዞ የነበረውን የሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ፉክክር መከላከያ እንዲቀላቀል ካስቻሉ ተጫዋቾትም አንዷ ነበረች፡፡ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ያሳየው የኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች ብሄራዊ ቡድንም አምበል ነበረች፡፡

[/restab]
[restab title=”የአምና ሽልማት”]

በ2007 በተደረገው ምርጫ ከ1-15 ደረጃዎችን የያዙት ግለሰቦች እና ተቋማት
(70% የሶከር ኢትዮጵያ ኤዲተሮች እንዲሁም 30% የአንባብያን ምርጫ ድምር)

1.መሰረት ማኒ

2.ዋልያ ቢራ

3.ባህርዳር ስታየምና የከተማው ህዝብ

4.ዮሃንስ ሳህሌ

5.ሳሚ ሳኑሚ

6.ቅዱስ ጊዮርጊስ

7.ሎዛ አበራ

8.ጋቶች ፓኖም

9.አዳማ ከተማ

10.ፋሲል ተካልኝ እና ዘሪሁን ሸንታ

11. በኃይሉ አሰፋ

12. የሴቶች ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድን

13.ብስራት ኤፍ ኤም

14. ምንተስኖት አዳነ

15. ኑራ ኢማም

15. በአምላክ ተሰማ 

[/restab][/restabs]

Leave a Reply