ጋቦን 2017፡ ቱኒዚያ ሴኔጋልን ተከትላ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች

ለዋንጫ ከፍተኛ ግምት አግኝታ የነበረችው አልጄሪያ ከምድብ ሁለት ከዚምባቡዌ ጋር ተያይዛ ወድቃለች፡፡ ቱኒዚያ አስቀድማ ማለፏን ያረጋገጠችውን ሴኔጋልን ተከትላ ሩብ ፍፃሜ ደርሳለች፡፡ ሴኔጋል እና አልጄሪያ አቻ ሲለያዩ ስድስት ግቦች በተስተናገዱበት ጨዋታ ቱኒዚያ ዚምባቡዌን ረታለች፡፡

የጠበበ የማለፍ እድል የነበራት አልጄሪያ ከሴኔጋል ጋር 2-2 ተለያይታ ከምድብ መሰናበቷን አረጋግጣለች፡፡ የበረሃ ቀበሮዎቹ በጨዋታው ሁለት ግዜ መምራት ብትችልም የቴራንጋ አናብስቶቹ አቻ ለመሆን አልተቸገሩም፡፡ ኢስላም ስሊማኒ አልጄሪያ በ10ኛው ደቂቃ መሪ ሲያደርግ ፓፓ ኮሊ ዲዮፕ ብድኖቹ ወደ መልበሻ ክፍል ከማምራታቸው አስቀድሞ ሴኔጋልን አቻ አድርጓል፡፡ ስሊማኒ ዳግም አልጄሪን በ52ኛው ደቂቃ መሪ ቢያደርግም ከደቂቃ በኃላ ሙሳ ሶ የአቻነቷን ግብ አስቆጥሯል፡፡ ካፍ ኢስላም ስሊማኒን የጨዋታው ኮከብ ብሎ መርጧታል፡፡

ዚምባቡዌ ከዓመታት በኃላ የተመለሰችበትን የአፍሪካ ዋንጫ ከምድብ ተሰናብታለች፡፡ ቱኒዚያ ዚምባቡዌን 4-2 ማሸነፍ ችላለች፡፡ የካርቴጅ ንስሮቹ በነይም ሲሊቲ፣ የሱፍ ሳክኒ፣ ጠሃ ያሲን ከኔሲ እና ዋሂብ ካዝሪ (ፍ.ቅ.ም.) ግቦች በመጀመሪያው አጋማሽ 4-1 መምራት ችለዋል፡፡ ለጦረኞቹ አንድ ግብ ያስቆጠረው ኖሌጅ ሙሶና ነበር፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ በ58ተኛው ደቂቃ ቴንዳኢ ፓሽን ንዶሮ የዚምባቡዌን ሁለተኛ ግብ ማከል ችሏል፡፡ ጠሃ ያሲን ከኔሲ የጨዋታው ኮከብ ተብሎ ተመርጧል፡፡

ሴኔጋል ምድቡን በሰባት ነጥብ በመሪነት ስታጠናቅቅ ቱኒዚያ በስድስት ሁለተኛ ሆኗ ጨርሳለች፡፡ በሩብ ፍፃሜው ቡርኪናፋሶ ከቱኒዚያ እንዲሁም ሴኔጋል ከካሜሮን ይፋለማሉ፡፡

አላፉ ሃገር ባልተወቀበት ምድብ ሶስት ዛሬ ምሽት ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ የወቅቱ የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ ኮትዲቯር ከሞሮኮ እንዲሁም ቶጎ ከዲ.ሪ. ኮንጎ ይጫወታሉ፡፡ ጨዋታዎቹ ምሽት 4፡00 ይጀምራሉ፡፡

የፎቶ ምንጭ: BackpagePix

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *