የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ዳዊት እስጢፋኖስ ጅማ አባጅፋርን ተቀላቅሏል፡፡
በተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በንቃት ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ጅማ አባጅፋር ዳዊትን እስጢፋኖስን አስፈረመ፡፡ የቀድሞው የባንክ፣ ደደቢት፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ኤሌክትሪክ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ፋሲል ከነማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ለሁለተኛ ጊዜ የተቀላቀለው መከላከያን ከለቀቀ በኋላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በሰበታ ከተማ አሳልፏል፡፡ ከሰበታ ጋር ውሉን በማገባድም ጉዞውን ወደ ጅማ አባ ጅፋር አድርጓል።
ዳዊት በጅማ ከዚህ ቀደም በቡና እና ሰበታ አብሮት ከተጫወተው መስዑድ መሐመድ ጋር በድጋሚ የሚገናኝ ይሆናል ፡፡