ሲዳማ ቡና ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ደብዳቤውን አስገብቷል።
ከቀናት በፊት የክለቦች ክፍያ ስርዓት አስተዳደር ጥሷል ተብሎ ቅጣት የተጣለበት ሲዳማ ቡና ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ደብዳቤ አስገብቷል።
በስድስት ተጫዋቾች ጉዳይ ተከሶ አስራ ስምንት ሚልዮን ብር እንዲቀጣና ሌሎች ቅጣቶች የተጣለበት ቡድኑ የክለቡ ሥራ አመራር ቦርድ አስቸኳይ ስብሰባ ካደረገ በኋላ በቂ እና አሳማኝ ማስረጃ ማቅረቡን በመግለፅ ውሳኔው ህግ እና የቅን ልቦና መርህን ያልተከተለ መሆኑ ጠቅሶ ይግባኝ እንደሚጠይቅ የገለፀበትን ደብዳቤ ለፌዴሬሽኑ አስገብቷል።