“በምርመራው ሂደት ሦስት ጋዜጠኞች ስማቸው ተይዟል” አቶ ክፍሌ ሰይፈ

“በምርመራው ሂደት ሦስት ጋዜጠኞች ስማቸው ተይዟል” አቶ ክፍሌ ሰይፈ

የክለቦች የፋይናንስ አስተዳደርን በተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጥ ሦስት የሀገራችን ጋዜጠኞች በዚህ ህገወጥ የዝውውር ክፍያ ስማቸው እንደተገኘ ተገልጿል።

ዘንድሮ እየተተገበረ በሚገኘው የክለቦች የፋይናንስ አስተዳደርን በተመለከተ ማብራሪያ እየሰጠ የሚገኘው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር እጅግ ውስብስብ በሆነው የማጣራት ሂደት ውስጥ በሦስተኛ ወገን ከተፈፀሙ የዝውውር ክፍያዎች የሦስት ጋዜጠኞች ስም እንደተገኘ ተገልጿል።

የአክሲዮን ማኅበሩ የበላይ ኃላፊዎች ይህንን ይበሉ እንጂ የጋዜጠኞችን ስም ከማንሳት ተቆጥበዋል።