“በ2 ክለቦች እና በ10 ተጫዋቾች ሌላ ምርመራ እየተደረገ ነው”

“በ2 ክለቦች እና በ10 ተጫዋቾች ሌላ ምርመራ እየተደረገ ነው”

በአራት ክለቦች እና በ16 ተጫዋቾች ላይ ከተደረገው ውሳኔ በተጨማሪ በሌሎች 2 ክለቦች እና በ10 ተጫዋቾች ከፍተኛ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ከተለያዩ አካላት ተወጣጥተው የተቋቋመው ኮሚቴ በክለቦች የፋይናንስ አስተዳደር የወሰነውን ውሳኔ በተመለከተ ማብራሪያ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ባሳለፍነው ሰኞ ክለቦች እና ተጫዋቾች ላይ ከተወሰነው ውሳኔ በተጨማሪ ሁሉም ክለቦች ላይ ማጣራት እየተደረገ እንደሚገኝ ቢነሳም በዋናነት በሁለት ክለቦች እና በአስር ተጫዋቾች ላይ ሰፊ ማጣራት እየተደረገ እንደሚገኝ ተመላክቷል።

አሁን ላይ ውሳኔ የተላለፈባቸው ተጫዋቾች ሒሳባቸው ለምን አልታገደም በሚል ለተነሳው ጥያቄ ያላሳገድነው የመጨረሻ የይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የመጨረሻ ፍርድ እስኪሰጥ ነው። ለአሁኑ የወሰድከውን በ7ቀን ውስጥ መልስ ካልሆነ አትጫወትም ነው።