“…አትፈፅሙም ብሎ በጉልበት የሚገዳደረን አካል ካለ ትተን እንሄዳለን።” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

“…አትፈፅሙም ብሎ በጉልበት የሚገዳደረን አካል ካለ ትተን እንሄዳለን።” መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ

የአክሲዮን ማኅበሩ የቦርድ ሰብሳቢ ከሰሞኑ መነጋገሪያ የሆነውን ጉዳይ በተመለከተ እየሰጡ በሚገኙበት ሰዓት የአፈፃፀም ሂደቱን በተመለከተ ያሉት ሀሳብ አለ።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሰብሳቢ መቶ አለቃ ፍቃደ ማሞ የተወሰነው ውሳኔ በቁርጠኝነት የማስፈፀሙን ሂደት በተመለከተ ማብራሪያ ሲሰጡ “እስካሁን እዚህ ደርሰናል ፤ ከዚህ በኋላ ያለውን ተጋግዘን እንሰራለን። በሚገባ እናስፈፅማለን። አትፈፅሙም ብሎ በጉልበት የሚገዳደረን አካል ካለ ትተን እንሄዳለን።” ብለዋል።

ጉዳዩ በኢትዮጵያ ፌዴሬሽን መተዳደሪያ ደንብ ቀጣይ አቅጣጫው እንደሚታይ ገልፀው በኮሚቴው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የዲሲፕሊን ኮሚቴ አባል ስላለ ክለቦች አቤቱታቸውን ለይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ እንደሚያስገቡ አመላክተዋል። መቶ አለቃ ጨምረውም “ቅር የሚያስኝ የአሰራር ስህተት የሰራን አይመስለንም።” ካሉ በኋላ እዚህ ብንረታ እንኳን ጉዳዩን ወደ ካስ ይዘን እንሄዳለን ብለዋል።

የቦርድ ሰብሳቢው ጨምረው “ተጫዋቾችም ካስ እና ፊፋ ድረስ ሄደው መጠየቅ ይችላሉ። አሠራራችን የፊፋን ፕሮሲጀር ተከትሎ የሄደ ነው” በማለት ሀሳባቸውን አጋርተዋል።