ዳንኤል ፀሃዬ ደደቢትን እስከ አመቱ መጨረሻ ድረስ ያሰለጥናሉ

አሰልጣኝ ዮሃነስ ሳህሌን ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አሰሳልፎ የሰጠው ደደቢት በምክትል አሰልጣኙ ዳንኤል ፃሃዬ መሪነት የውድድር ዘመኑን እንደሚያጠናቅቅ አስታቋል፡፡

የቀድሞው የጉና ንግድ የመስመር ተከላካይ ካለፈው አመት መጀመርያ ጀምሮ የደደቢት ምክትል አሰልጣኝ ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የአሰልጣኝ ማርያኖ ባሬቶ ምክትል ሆነውም አገልግለዋል፡፡

ደደቢት በሊጉ 6 ወሳኝ ጨዋታዎች የሚቀሩት ሲሆን የቻምፒዮንነት ተስፋውም አልተሟጠጠም፡፡ አሰልጣኝ ዳንኤል በቀሪዎቹ ጨዋታዎች በደደቢት የሚያስመዘግቡት ውጤትም በቀጣይ አመት በቋሚነት የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሆነው ለመቀጠል ወሳኝ ይሆናል ተብሏል፡፡

አሰልጣኙ በዛሬው የዮሃንስ ሳህሌ ሽኝት ላይ በሰጡት አስተያየት በጊዜያዊ አሰልጣኝነቱ ሹመት ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ