ኢትዮጵያዊው ግራ ተመላላሽ አበባው ቡጣቆ ከሱዳኑ ሃያል ክለብ አል ሂላል ጋር በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ በስኬታማነቱ ቀጥሏል፡፡ የአበባው ክለብ ሂላል ባሳለፍነው ዕሁድ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ክለብ የሆነውን ሳንጋ ባሌንዴን አሸንፎ የምድብ ማጣሪያውን ተቀላቅሏል፡፡ ዛሬ በግብፅ ካይሮ በወጣው የምድብ ድልድል ሂላል በምድብ አንድ ከግብፁ ሰሞሃ፣ ከሞሮኮው መግርብ ትቱዋ እና ከሃያሉ የኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ክለብ ቲፒ ማዜምቤ ጋር ተገናኝቷል፡፡ አበባው በምድብ ማጣሪያው መጫወት ከቻለ በአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ድልድል የተጫወተ የመጀመሪው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች መሆን ይችላል፡፡
በተያያዘ ዜና የሳላዲን ሰዒዱ አል አሃሊ በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ከቱኒዚያው ክለብ አፍሪካን ጋር የሚጋጠም ይሆናል፡፡
ያጋሩ