አበባው ቡታቆ ከአል ሂላል ጋር ተለያየ

የሱዳኑ ታላቅ ክለብ አል ሂላል ኢትዮጵያዊው የመስመር ተከላካይ አበባው ቡታቃን መልቀቃቸውን ዛሬ ይፋ አድርገዋል፡፡

አበባው በክረምት የዝውውር መሰስኮት ቅዱስ ጊዮርጊስን ለቆ ወደ ሱዳን ካመራ ወዲህ በክለቡ ቋሚ ተሰላፊነትን ማግኘት ያልቻለ ሲሆን ክለቡን ለመልመድ እንደተቸገረም ተነግሯል፡፡

ክለቡ ከደቂዎች በፊት እንዳስታወቀው ማሊያዊው ሱሌይማን ኮናቴ እና አበባው ቡታቆ ለክለቡ በቂ ግልጋሎት መስጠት ባለመቻላቸው ለመልቀቅ እንደወሰኑ ከመግለፁ ውጪ የተብራራ መግለጫ አላወጣም፡፡

ያጋሩ