ዘሪሁን ቢያድግልኝ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋና ፀኃፊ ሆነው ተሾሙ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ያወጣውን የስራ ማስታወቂያ ተከትሎ የአመልካቾችን የትምህርት እና የስራ ልምድ ተመልክቶ በመጨረሻ አቶ ዘሪሁን ቢያድግልኝን የፌዴሬሽኑ ዋና ፀሃፊ አድርጎ ሾሟል፡፡

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ባለፈው ሰኔ ወር ኢትዮጵያ በፊፋ እንድትቀጣ ያደረጋትን ያልተገባ ተጫዋች በማሰለፏ በተነሳ ውዝግብ ዋና ፀሃፊው አቶ አሸናፊ እጅጉ ከሃላፊነታቸው ከተነሱ በኋላ አቶ ይግዛውላለፉት 9 ወራት የአቶ አሸናፊን ቦታ በጊዜያዊነት ይዘው መቆየታቸው ይታወሳል፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ዋናፀሃፊ አቶ ዘሪሁን ቢያድግልኝ ላለፉት በርካታ አመታት ከኢትዮጵያ እግርኳስ ጋር የተቆራኙ ባለሙያ ናቸው፡፡ አቶ ዘሪሁን በስፖርት ሳይንስ ሁለተኛ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን በተለያዩ የስፖርት ተቋማት ውስጥ በከፍተኛ የሃላፊነት ቦታ አገልግለዋል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ