መብራት ኃይል ከ ኢትዮጵያ መድን – ዳሰሳ

ቀን – ቅዳሜ 08 የካቲት 2006

ቦታ – አበበ ቢቂላ ስታዲየም

የጨዋታ መጀመርያ ሰአት – 08፡00

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 11ኛ ሳምንት በሁለቱ የዋና ከተማ ቡድኖች ጨዋታ ይጀመራል፡፡ ዘንድሮ በሊጉ ደካማ ሆነው የቀረቡት ሁለቱ ቡድኖች መሸናነፍ አንደኛውን ከአደጋው ዞን ለመውጣት ሲያግዝ ሌላኛውን በወራጅ ቀጠናው እንዲዳክር ያደርገዋል፡፡

የሊጉ አናት ላይ እንደተጠበቀው ፉክክር አለመኖሩ ከወገቡ በታች ያሉት ቡድኖች ጨዋታ ይበልጥ ትኩረት እንዲስብ አድርጎታል፡፡ የአስራት ኃይሌው መድን ባለፈው ሰኞ ወላይታ ዲቻን አስተናግዶ ካለግብ አቻ ሲለያይ መብራት ኃይል በበኩሉ በቀድሞ አምበላቸው በተቆጠረች ብቸኛ ግብ 1-0 ተሸንፎ ከጎንደር ተመልሷል፡፡

ጨዋታው በአበበ ቢቂላ የሚካሄድ በመሆኑ ለትራንስፖርት አመቺ ባይሆንም ይህንን ግጥሚያ ተከትሎ ከሚደረገው ጨዋታ ትልቅነት አንፃር ጨዋታው ተመልካች ያገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ጠቃሚ ነጥቦች

መብራት ኃይል በ6 ነጥብ የሊጉ የመጨረሻ ደረጃን ሲይዝ መድን በበኩሉ በ7ነጥቦች 12ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች ዘንድሮ ሲገናኙ ለ2ኛ ጊዜ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ጨዋታ ላይ ተገናኝተው ሳይሸናነፉ 1-1 መለያየታቸው ይታወሳል፡፡

መብራት ኃይል በሊጉ በጥሎ ማለፉ እና በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ባደረጋቸው ያለፉት 13 ተከታታይ ጨዋታዎች ምንም ድል አላስመዘገበም፡፡

የእርስ በእርስ ግንኙነቶች

ተጫወቱ – 22

መብራት ኃይል አሸነፈ – 15

አቻ – 4

ኢትዮጵያ መድን አሸነፈ – 3

መብራት ኃይል አስቆጠረ – 38

ኢትዮጵያ መድን አስቆጠረ – 17

{jcomments on}

ያጋሩ