ኢትዮጵያ ቡና ከመሪው ጋር ያለውን ልዩነት አጥብቦ አንደኛውን ዙር አጠናቀቀ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተስተካካይ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሐረር ቢራን 2-0 አሸንፎ አንደኛውን ዙር በሁለተኝነት አጠናቋል፡፡

ጨዋታው ያን ያህል ቀልብ ሳቢ ያልበረ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና በኳስ ቁጥጥር የተሸሉ ነበሩ፡፡

በአንደኛው አጋማሽ የመጀመርያዎቹ ደቂቃዎች ኢትዮጵያ ቡናዎች በአስቻለው ግርማ እና ኤፍሬም አሻሞ አማካኝነት ለግብ የቀረቡ ሙከራዎች ማድረግ ቢችለም የመጀመርያ ግባቸውን ለማግኘት ግማሽ ሰአት ጠብቀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ቡና መሪ መሆን የቻለው በ32ኛው ደቂቃ ወደ ጥሩ አቋሙ በተመለሰው ኤፍሬም አሻሞ አማካኝነት ነው፡፡ ኤፍሬም በቀድሞ ክለ ቡ ላይ ያስቆጠራት ግብ በዘንድሮ ፕሪሚየር ሊግ ያስቆጠራቸውን ግቦች መጠን ወደ 6 እንዲያሳድግ አስችሎታል፡፡

ከግቧ መቆጠር በኋላ ሐረር ቢራዎች አቻ ለመሆን የሚያስችሉ ወርቃማ እድሎች ቢያገኙም መጠቀም ሳይችሉ የመጀመርያው አጋማሽ በቡና 1-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

ከእረፍት መልስ ኢትዮጵያ ቡናዎች የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ቢኖራቸውም የግብ እድሎች በመፍጠር በኩል ደክመው ቀርበዋል፡፡ በ68ኛው ደቂቃ ሰለሞን ገብረ መድህን የኢትዮጵያ ቡናን መሪነት ወደ ሁለት ከፍ ካደረገባት ግብ ውጪም የሚቀሱ ሙከራዎች አልተስተዋሉም፡፡

ኢትዮጵያ ቡናዎች የምሽቱን የሐረር ቢራ ድል ጨምሮ 6 ተከታታይ ጨዋታዎችን በድል የተወጡ ሲሆን ከ2 ወር በፊት ከነበሩበት የደረጃ ሰንጠረዡ ወገብ በእጅጉ አንሰራርተው 28 ነጠቦችን በመሰብሰብ 1ኛውን ዙር በ2ኝነት አጠናቀዋል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉ 1ኛ ዙር ተስተካካይ ጨዋታዎች ነገ እና ሰኞ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጠናቀቅና ከ9 ቀናት እረፍት በኋላ ሁለተኛ ዙር ሚያዝያ 8 ይጀመራል፡፡

{jcomments on}

ያጋሩ