ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት 

​​FTኢት. ንግድ ባንክ  1 4 ቅዱስ ጊዮርጊስ

11′ አቡበከር ሳኒ 24′ አዳነ ግርማ (P) 33′ 39′ ሳልሀዲን ሰይድ |45+1 ፒተር ንዋድኬ

ጨዋታው ተጠናቋል !

91′ አዳነ ግርማ ከመሀል ሜዳ የተላከለትን ኳስ ለማስቆጠር ባደረገው ጥረት ከ ሙሴ እና ከ ቶክ ጀምስ ጋር ተጋጭተዋል ። ቶክ ጀምስ በግጭቱ ጉዳት ደርሶበት ለህክምና እርዳታ ከሜዳ ወጥቷል ።

90′ ሳልሀዲን ባርጌቾ ቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

90′ ጭማሪ ደቂቃ 3 !

87′ ዳንኤል ለታ ከፒተር ንዋድኬ የተቀበለውን ኳስ በቀጥታ ለማስቆጠር ቢሞክርም ሳልሀዲን ባርጌቾ ተደርቦ መልሶበታል ።

81′ የተጨዋች ቅያሪ ቅ/ጊዮርጊስ 

ተስፋዬ አለባቸው በበሀይሉ አሰፋ ተቀይሮ ወደሜዳ ገብቷል ።

73′ ጨዋታው ጊዜ በገፋ ቁጥር እየተቀዛቀዘ መጥቷል ። ከሜዳ ላይ እንቅስቃሴ ይልቅ የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎች የድጋፍ ዜማ አዝናኝ እየሆነ ነው።

69′ የተጨዋች ቅያሪ ቅ/ጊዮርጊስ

ምንያህል ተሾመ ገብቶ ሳልህዲን ሰይድ ወጥቷል ። የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊዎች ለተጨዋቹ ያላቸውን አድናቆት በዝማሬ ገልፀዋል ።

67′ ፒተር ኑዋድኬ ከኤፍሬም ካሳ የተቀበለውን ኳስ ከፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውጪ ቢሞክርም ፍሬው በቀላሉ ይዞበታል ።

63′ አዳነ ግርማ በሙሴ አናት ላይ ወደግብ የላካት ኳስ 5ተኛ ግብ ሆነች ተብሎ ሲጠበቅ ተቀይሮ የገባው ፍቃዱ ደነቀ ከመስመር ላይ አውጥቷታል ።

63′ የተጨዋች ቅያሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 

ፍቃዱ ደነቀ በአንተነህ ገ/ክርስቶስ ምትክ ወደሜዳ ገብቷል 

59′ ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች በተሻለ ወደ ግብ መቅረብ ጀምረዋል ።

53′ ከመጀመሪያው አጋማሽ ጋር ሲነፃፀር ጨዋታው በእንቅስቃሴ ደከም ብሏል ።

51′ የተጨዋች ቅያሪ ቅ/ጊዮርጊስ

ፍሬዘር ካሳ ምንተስኖት አዳነን ተክቶታል ። ቅያሪው የጉዳት ነው ።

46′ የተጨዋች ቅያሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
አምሀ በለጠ ወጥቶ ሳሙኤል ዮሀንስ ገብቷል

ሁለተኛው አጋማሽ ተጀምሯል !

የመጀመሪያው ግማሽ ተጠናቋል !

45+1 ጎል !!! ፒተር ንዋድኬ
ቅጣት ምቱን ፒተር ወደጎልነት ቀይሮታል።

45′ አስቻለው ታመነ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ጠርዝ ላያ ፒተር ላይ በፈፀመው ጥፋት የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

42′ ቅ/ጊዮርጊሶች አሁንም በተለይ በሀይሉ አሰፋ ባለበት የቀኝ መስመር ጥቃት እየሰነዘሩ ነው ።

39′ ጎል !!!! ሳልሀዲን ሰይድ  ቅ/ጊዮርጊስ

ምንተስኖት አዳነ ከመስመር ያሻማውን ኳስ ቶክ ጀምስ ለማውጣት ሲሞክር ኳስ ወደግቡ ሄዳ አግዳሚውን ገጭታ ስትመለስ ሳልሀዲን አግኝቶ አስቆጥሯል ።

35′ ፒተር ንዋድኬ በግምት ከ 20 ሜትር ርቀት የሞከረው ኳስ ወደላይ ተነስቷል ።

33′ ጎል ሳልሀዲን ሰይድ ቅ/ጊዮርጊስ

አቡበከር ሳኒ ከግራ መስመር ያሻማው ኳስ በምንተስኖት ተጨርፎ ሳልሀዲን ጋር ሲደርስ ሳልሀዲን አንድ ተከላካይ በማለፍ ከግቡ ጥቂት ሜትር ርቀት ላይ በመምታት አስቆጥሯል ።

31′ የተጨዋች ለውጥ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

አዲሱ ሰይፉ ወጥቶ ዳንኤል ለታ ገብቷል

26′ ከጎሉ መቆጠር በኃላም የጊዮርጊሶች የበላይነት በጨዋታው እንደቀጠለ ነው ።

24′ ጎል !!! ቅ/ጊዮርጊስ አዳነ ግርማ

አዳነ ግርማ ፍፁም ቅጣት ምቱን ሁለተኛ ጎል አድርጎታል !

23′ ሙሴ ግ/ኪዳን በሀይሉ አሰፋ ላይ በሰራው ጥፋት ቅ/ጊዮርጊስ የፍፁም ቅጣት ምት አገኘ !ሙሴ የቢጫ ካርድ ተመልክቷል ።

22′ ሳልሀዲን ሰይድ ምንተስኖት ከመሀል ሜዳ የጣለለትን ረጅም ኳስ ቺፕ ለማረግ ሲሞክር ወደላይ ተነስቶበታል ።

18′ ጨዋታው በተወሰነ መልኩ በተቀዛቀዘ ስሜት ውስጥ ይገኛል ።

15′ በአቡበከር ጎል ቀዳሚ የሆኑት የሊጉ መሪዎች ተጭነው እየተጫወቱ ይገኛሉ ። የጨዋታው አብዛኛው እንቅስቃሴም በንግድ ባንክ ሜዳ ላይ ሆኗል።

11′ ጎል !!! ቅ/ ጊዮርጊስ አቡበከር ሳኒ

አበባው ከግራ መስመር ያሻማውን የእጅ ውርወራ አቡበከር ይዞ በመግባት ግብ ጠባቂው ባጠበበት በኩል አስቆጥሯል ።

1′ ጨዋታው በኢትዮጽያ ንግድ ባንክ አማካይነት ተጀምሯል

 ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሰላለፍ 

29 ሙሴ ገ/ ኪዳን

15 አዲሱ ሰይፉ – 5 ቶክ ጀምስ – 16 ቢኒያም ሲራጅ – 13 አንተነህ ገብረክርስቶስ

80 ቢኒያም በላይ  – 8 ኤፍሬም ካሳ  – 6 አምሀ በለጠ

7 ዳንኤል አድሀኖም  – 11 ፒተር ንዋድኬ  – 21 ዮናስ ገረመው

ተጠባባቂዎች

33 ፋሪስ አለዊ

17 ሳሙኤል ዮሀንስ

99 ዳንኤል ለታ

26 ጌቱ ረፌራ

19 ፍቃዱ ደነቀ

12 አቤል አበበ

34 ሙሉቀን ተስፋዬ     

የቅዱስ ጊዮርጊስ አሰላለፍ                      

1 ፍሬው ጌታሁን

25 አንዳርጋቸው ይላቅ – 13 ሳላሀዲን ባርጊቾ – 15 አስቻለው ታመነ – 4 አበባዉ ቡጣቆ

26 ናትናኤል ዘለቀ – 23 ምንተስኖት አዳነ– 19 አዳነ ግርማ
  

16 በሀይሉ አሰፋ –  7 ሳላዲን ሰኢድ – 18 አቡበከር ሳኒ

ተጠባባቂዎች

22 ዘሪሁን ታደለ

14 ምንያህል ተሾመ

3 መሀሪ መና

2 ፍሬዘር ካሳ

12 ደጉ ደበበ

21 ተስፋዬ አለባቸው 

20 ዘካሪያስ ቱጂ

ያለፉት 3 ጨዋታዎች ውጤት

ኢት. ንግድ ባንክ | አሸነፈ | አቻ | ተሸነፈ

ቅዱስ ጊዮርጊስ | አቻ | አሸነፈ | አቻ


ግንኙነት
ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ሲገናኙ ይህ ለ34ኛ ዜ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም ባደረጉት 33 ግንኙነቶች ቅዱስ ጊዮርጊስ 21 ሲያሸንፍ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3 አሸንፏል፡፡ 3 ጊዜ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡


ደረጃ
ቅዱስ ጊዮርጊስ 26 ነጥቦችን በመሰብሰብ 1ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ንግድ ባንክ በ12 ነጥቦች 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡


ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን!

በ15ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ የሚያደርጉትን ጨዋታ በዚህ ገፅ ላይ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

4 Comments

  1. በጣም ጥሩ አቀረረብ ነው አሰላለፉን አስቀድማቹህ ብታሳውቁን መልካም ነው በርቱ

    1. wow modern system for ethio f.ball manchester,arsenal chealsea.nothing for me am ethiopian they dont no me also i dont know them bravo socer ethiooia i proud ….

Leave a Reply