ደደቢት ከ ወላይታ ድቻ | ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት 

​​FTደደቢት 3-0 ወላይታ ድቻ

20′ አቤል እንዳለ 23′ ጌታነህ ከበደ 62′ ሽመክት ጉግሳ


ተጠናቀቀ!
ጨዋታው በደደቢት 3-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ፡፡

90+4′ ጌታነህ ተከላካይ አልፎ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የሞከረውን ኳስ ወንድወሰን አውጥቶታል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 4

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
84′ ሳምሶን ጥላሁን ወጥቶ የአብስራ ተስፋዬ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ድቻ
74′ ጸጋዬ ብርሃኑ ወጥቶ ዮርዳኖስ ዮሃንስ ገብቷል፡፡

73′ አናጋው ባደግ ከበዛብህ ጋር በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ሳጥጥ ገብቶ የሞከረውን ክሌመንት በቀላሉ ይዞበታል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
71′ ኤፍሬም አሻሞ ወጥቶ እያሱ ተስፋዬ ገብቷል፡፡

66′ የመሳይ አንጪሶን ፍጹም ቅጣት ምት ክሌመንት አዞንቶ አድኖታል፡፡ የተመለሰውን ኳስ ዳግም ንጉሴ መትቶ የግቡ አግዳሚ መልሶበታል፡፡

65′ ፍጹም ቅጣት ምት ለወላይታ ድቻ !

ጎልልል!!!! ደደቢት
62′ ሽመክት ጉግሳ ተጫዋቾችን አልፎ በግሩም ሁኔታ በግራ እግሩ አክርሮ የመታው ኳስ በድቻ መረብ ላይ አርፏል፡፡

60′ ወላይታ ድቻ ሙሉ ብልጫ በመውሰድ ጫና ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ደደቢት
57′ አቤል እነንዳለ ወጥቶ ካድር ኩሊባሊ ገብቷል፡፡

የተጫዋች ለውጥ – ድቻ
55′ ዮሴፍ ድንገቱ ወጥቶ ቶማስ ስምረቱ ገብቷል፡፡

53′ ጌታነህ ከበደ የሞከረውን ኳስ ወንድወሰን ይዞበታል፡፡

ተጀመረ!
የሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጀምሯል፡፡

የእረፍት ሰአት ለውጥ – ድቻ
አማኑኤል ተሾመ ወጥቶ መሳይ አንጪሶ ገብቷል፡፡

እረፍት!
የመጀመርያው አጋማሽ በደደቢት 2-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ደቂቃ – 2

41′ አማኑኤል ተሾመ ከርቀት የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

35′ ሁለቱም ቡድኖች በተደጋጋሚ ወደ ግብ በመድረስ የግብ እድል ለመፍጠር በሚያደርጉት ጥረት ጨዋታው ተሟሙቆ ቀጥሏል፡፡

ጎልልል! ደደቢት
23′ ጌታነህ ከበደ ግብ ጠባቂውን በማለፍ የደደቢትን ሁለተኛ ጎል አስቆጥሯል፡፡

ጎልልል!!! ደደቢት
20′ ጌታነህ ከበደ ከ2ኛ ቅጣት ምት የሞከረው ኳስ በወንድወሰን ሲመለስ አቤል እንዳለ አግኝቶ ወደ ግብነት ቀይሮታል፡፡

13′ ጌታነህ ከበደ ከርቀት የሞከረውን ኳስ ወንድወሰን አውጥቶበታል፡፡

10′ ጨዋታው በፈጣን እንቅስቃሴ እና የድቻ ደጋፊዎች ማበረታቻ ድጋፍ ሞቅ ብሎ እየተደረገ ይገኛል፡፡

5′ ፀጋዬ ብርሃኑ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ የሞከረው ኳስ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡ የሚያስቆጭ አጋጣሚ!

1′ ሽመክት ጉግሳ የሞከረው ኳስ ኢላማውን ሳይጠብቅ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

ተጀመረ!
ጨዋታው በ1 ደቂቃ የህሊና ጸሎት በደደቢት አማካኝነት ተጀምሯል፡፡

የደደቢት አሰላለፍ

33 ክሌመንት አዞንቶ

7 ስዩም ተስፋዬ – 6 አይናለም ኃይለ – 14 አክሊሉ አየነው – 10 ብርሃኑ ቦጋለ

8 ሳምሶን ጥላሁን – 4 አስራት መገርሳ – 18 አቤል እንዳለ

19 ሽመክት ጉግሳ – 9 ጌታነህ ከበደ – 21 ኤፍሬም አሻሞ

ተጠባባቂዎች
22 ታሪክ ጌትነት
11 አቤል ያለው
16 ሰለሞን ሐብቴ
27 እያሱ ተስፋዬ
24 ካድር ኩሊባሊ
20 የአብስራ ተስፋዬ
15 ደስታ ደሙ

የወላይታ ድቻ አሰላለፍ

1 ወንድወሰን አሸናፊ

2 ፈቱዲን ጀማል – 20 አብዱልሰመድ አሊ – 27 ሙባረክ ሽኩር – 5 ዳግም ንጉሴ

7 አናጋው ባደግ – 4 ዮሴፍ ድንገቱ – 8 አማኑኤል ተሾመ

17 በዛብህ መለዮ – 19 አላዘር ፋሲካ – 23 ጸጋዬ ብርሃኑ

ተጠባባቂዎች

99 ወንድወሰን ገረመው
6 ተክሉ ታፈሰ
3 ቶማስ ስምረቱ
28 መሳይ አንጪሶ
14 ጥላሁኔ በቶ
15 ዮርዳኖስ ዮሃንስ
11 ፉአድ ተማም

09:40 ሁለቱ ቡድኖች ሜዳ ገብተው በማማሟቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

ያለፉት 5 ጨዋታዎች ውጤት

ደደቢት | አሸነፈ | አቻ | ተሸነፈ

ወላይታ ድቻ | ተሸነፈ | አቻ | አቻ

ግንኙነት

ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ ሲገናኙ ይህ ለ7ኛ ጊዜ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም በነበራቸው 6 ግንኙነቶች ደደቢት 4 ሲያሸንፍ ፤ ወላይታ ድቻ 2 አሸንፏል፡፡

ደረጃ

ደደቢት 24 ነጥቦችን በመሰብሰብ 3ኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ ወላይታ ድቻ በ17 ነጥቦች 10ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ጤና ይስጥልኝ ክቡራት እና ክቡራን!

በ15ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ደደቢት ከ ወላይታ ድቻ አበበ ቢቂላ ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታ በዚህ ገፅ በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ወደ እናንተ እናደርሳለን፡፡

መልካም ቆይታ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር!

 

Leave a Reply