የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ሆነ

የ2009 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ውድድር እጣ ማውጣ ስነስርአት ዛሬ በሶዶ ከተማ ተካሂዷል፡፡ 21 ክለቦች በሚሳተፉበት ውድድር 11 ክለቦች ባለፈው አመት በነበራቸው ደረጃ መሰረት በቀጥታ ወደ ተከታዩ ዙር ሲያልፉ 10 ክለቦች በአንደኛው ዙር ጨዋታ አድርገው 5 ቡድኖች ወደ 2ኛው ዙር ያልፋሉ፡፡

በመጀመርያው ዙር 5 የከፍተኛ ሊግ እና 5 የፕሪምየር ሊግ ቡድኖች ተሳታፊ የሚሆኑ ሲሆን በውድድሩ እንደሚሳተፍ አሳውቆ የነበረው አክሱም ከተማ እንደማይሳተፍ በመረጋገጡ ሽረ እንዳስላሴ ቦታውን ተክቶ ገብቷል፡፡

የመጀመርያው ዙር ጨዋታዎች የካቲት 11 እና 12 የሚደረጉ ሲሆን ከ2ኛ ዙር ጀምሮ የሚደረጉ ጨዋታዎች ክፍት ጊዜዎች እየተፈለጉ በውድድሮች መካከል አልያም በውድድሮች መጨረሻ ለማድረግ ታቅዷል፡፡ የጊዜ እጥረት የሚያጋጥም ከሆነም ውድድሩን ማስቀረት እንደ አማራጭ ተይዟል፡፡

* ሁሉም ጨዋታዎች የሚደረጉት አዲሰ አበባ ላይ ነው፡፡

የ1ኛ ዙር ተጋጣሚዎች

[የጨዋታ ቁጥር] ተጋጣሚዎች

[1] አራዳ ክፍለከተማ ከ ወልድያ

[2] ኢትዮጵ ውሃ ስፖርት ከ አዲስ አበባ ከተማ

[3] ሽረ እንዳስላሴ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ

[4] ድሬዳዋ ፖሊስ ከ ፋሲል ከተማ

[5] ፌዴራል ፖሊስ ከ ጅማ አባ ቡና

የ2ኛ ዙር ተጋጣሚዎች

[6] ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ድሬዳዋ ከተማ

[7]  መከላከያ ከ ሀዋሳ ከተማ

[8] ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ ወልድያ እና አራዳ ክፍለከተማ አሸናፊ

[9] የፋሲል ከተማ እና ድሬዳዋ ፖሊስ አሸናፊ ከ አዳማ ከተማ

[10] ደደቢት ከ ፌዴራል ፖሊስ እና ጅማ አባ ቡና አሸናፊ

[11] የአአ ከተማ እና ውሃ ስፖርት አሸናፊ ከ ሲዳማ ቡና

[12] ወላይታ ድቻ ከ አርባምንጭ ከተማ

[13] የሽረ እንዳስላሴ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ አሸናፊ ከ ኢትዮጵያ ቡና

ሩብ ፍጻሜ

[14] የጨዋታ 6 አሸናፊ ከ ጨዋታ 7 አሸናፊ

[15] የጨዋታ 8 አሸናፊ ከ ጨዋታ 9 አሸናፊ

[16] የጨዋታ 10 አሸናፊ ከ ጨዋታ 11 አሸናፊ

[17] የጨዋታ 12 አሸናፊ ከ ጨዋታ 13 አሸናፊ

ግማሽ ፍፃሜ

[18] የጨዋታ 14 አሸናፊ ከ ጨዋታ 15 አሸናፊ

[19] የጨዋታ 16 አሸናፊ ከ ጨዋታ 17 አሸናፊ

ፍጻሜ

[20] የጨዋታ 18 አሸናፊ ከ ጨዋታ 19 አሸናፊ

Leave a Reply