አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ ከኤሌክትሪክ ተሰናበቱ

በመውረድ ስጋት ውስጥ የሚገኘው ኤሌክትሪክ አሰልጣኙ አጥናፉ አለሙን ማሰናበቱን ተወዳጁ ጨዋታ ዘግቧል፡፡

የቡልጋሪያዊውን ዮርዳን ስቶይኮቭ ስንብት ተከትሎ ከዋና ከረዳት አሰልጣኝነት ወደ ዋና አሰልጣኝነት ያደጉት አሰልጣኝ አጥናፉ አለሙ በዘንድሮው የውድድር ዘመን ያስመዘገቡት ደካማ ውጤት ለስንብታቸው መንስኤ ነው ተብሏል፡፡

የአሰልጣኙን ስንብት ተከትሎ የኤሌትሪክ ተስፋ ቡድን አሰልጣኝ የሆነው ኤርሚያስ በቀሪዎቹ 3 የሊግ ጨዋታዎች እና የጥሎ ማለፍ ግጥሚያዎች ላይ ኤሌክትሪክን ይመራል ተብሏል፡፡

ኤሌክትሪክ 3 ጨዋታ በሚቀረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ24 ነጥቦች 12ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ያጋሩ