የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የፕሌይ ኦፍ ጨዋታዎች ነገ ይጀመራሉ

የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ወደ ወሳኙ የፕሌይ ኦፍ ፍጥጫዎች ረሸጋግሯል፡፡ በሁለት ዞኖች ተከፍሎ ሲካሄድ የሰነበተው የ2006 የውድድር ዘመን ከየዞኑ ከ1-4 በወጡ 8 ቡድኖች መካከል በሀዋሳ ከተማ አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡

ከማእከላዊና ሰሜን ዞን የአምናው ቻምፒዮን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመሪነት ሲጨርስ ደደቢት በ2ኝነት ፣ ዳሽን ቢራ በ3ኝነት እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ በ4ኝነት አጠናቀዋል፡፡

በምስራቅ እና ደቡብ ዞን ደግሞ ምንም ጨዋታ ያልተሸነፈው ሀዋሳ ከነማ በአንደኝነት ሲጨርስ ሲዳማ ቡና በ2ኝነት ፣ ድሬዳዋ ከነማ በ3ኝነት ፣ አርባምንጭ ከነማ በ4ኝነት አጠናቀው ወደ ፕሌይ ኦፍ ዙር አልፈዋል፡፡

8 ቡድኖችን በ2 ምድብ ከፍሎ የሚያፋልመው ውድድር ከዛሬ የምድብ ድልድሉ ይፋ እንደሚሆን ሲጠበቅ ከነገ ሰኔ 8 እስከ ሰኔ 22 ድረስ ጨዋታዎቹ ይደረጋሉ፡፡

ያጋሩ