​ከፍተኛ ሊግ፡ ሚዛን አማን መጠርያ ስያሜውን ሲለውጥ 9 ተጫዋቾችን አስፈርሟል

በኢትዮጵያ አንደኛ ሊግ ምድብ ሀ 1ኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ወደ ከፍተኛ ሊግ ያደገው ሚዛን አማን አደረጃጀቱን እና መጠርያ ስሙ ላይ ለውጥ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ክለቡ በአዲሱ ስያሜው ቤንች ማጂ ቡና ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የዞኑ አስተዳደር እና በስሩ የሚገኙ አስተዳድሮች እንዲሁም በቡና ዘርፍ የተሰማሩ የአካባቢው ባለሀብቶችን ለመሳብ በማሰብ ስያሜው መቀየሩም ተገልጿል፡፡

ክለቡ ለከፍተኛ ሊጉ ዝግጅት እያደረገ የሚገኝ ሲሆን 9 አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡ ኸይሩ ሙደሲር (ባቱ ከተማ)፣ ጃፋር ከበደ ( አምበሪቾ)፣ ሰለሞን መድህኔ (ነቀምት ከተማ)፣ ዳኛቸዉ አረጋ (ከሚዛን ቴፒ ዩንቨርስቲ የተገኘ)፣ ኦኬሎ ኦባንግ (ጋምቤላ ከተማ)፣ ዳዊት ታደለ (ቱሉ ቦሎ ከተማ)፣ ማቲያስ ሹመታ (አሶሳ ከተማ)፣ ፈሪድ ዩሱፋ (ጂማ ከተማ)፣ ይርጋለም አለሙ (ገላን ከተማ) ለክለቡ የፈረሙ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

(ዜና በዘርዓያዕቆብ ያዕቆብ – ከሚዛን አማን)

2 Comments

  1. I am Happy to see your picture here, I was the former player of Timihirt memiria, My name is Milkyas Bassa, I will help your team as much as possible in any aspects, concerning professional wise, Currently i have PhD degree in sport science and Football coaching Please contact me through email [email protected]

    Nice to see you again!
    Milkyas Bassa, PhD.
    Assistant Professor.

  2. የአካባቢውን ወጣቶች የመጠቀምን ሁኔታ ቢያጠናክር የበለጠ ውጤታማ ይሆናል።

Leave a Reply