ሽመልስ በቀለ እና ኢቲሃድ አሌክሳንድሪያ ሳይስማሙ ተለያዩ

 

የቀድሞው የሐዋሳ ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ አማካይ ሽመልስ በቀለ ከሱዳኑ አልሜሪክ ክለብ ጋር በስምምነት ከተለያየ በኋላ ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ እየተያያዘ ይገኛል።

ተጫዋቹ ከግብፁ ክለብ ኢቲሃድ አልክሳንድሪያ ጋር ድርድር ውስጥ ገብቶ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻሉም።

ሽመልስ “ለግብፁ ክለብ ኢቲሃድ አሌክሳንድሪያ እንደፈረምኩ የሚገልፁ ጭምጭምታዎች እውነት አይደሉም፤” ሲል በትዊተር አካውንቱ የገለፀ ሲሆን ክለቡም ድርድሩ መቋረጡን በዌብሳይቱ አስታውቋል።

እንደክለቡ መግለጫ ከሆነ ሽመልስ እና ኢቲሃድ በአብዛኛው ጉዳዮች ስምምነት ላይ መድረስ ቢችሉም ተጫዋቹ የኮንትራቱ 25% ገንዘብ በቅድሚያ እንዲከፈለው በመጠየቁና ክለቡ በዚህ ባለመስማማቱ ምክኒያት ድርድሩ ሊቋረጥ ችሏል።

ሽመልስ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ይገኛል።

 

ያጋሩ