ለኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 23 ተጫዋቾች ጥሪ ተደረገላቸው

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፍሬው ኃይለገብርኤል ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት እንዲረዳቸው ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።

በቅርቡ ከቡሩንዲ ጋር የመጀመርያ ዙር ጨዋታውን የሚያደረገው ብሔራዊ ቡድኑ ከሁለት ሳምንት በፊት ፍሬው ኃይለ ገብርኤል እና ህይወት አረፋይኔን በዋና እና ምክትል አሰልጣኝነት መቅጠሩ የሚታወስ ሲሆን ለጨወቻው የሚያደርገውን ዝግጅት ከታህሳስ 25 ጀምሮ እንደሚያከናውንም ይጠበቃል።

ፌዴሬሽኑ ይፋ ያደረገው የተጫዋቾች ዝርዝር

ግብ ጠባቂዎች
ዓባይነሽ ኤርቄሎ (ሀዋሳ ከተማ)፣ እምወድሽ ይርጋሸዋ (አዳማ ከተማ)፣ ምህረት ተሰማ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)

ተከላካዮች
ናርዶስ ጌትነት (አዳማ ከተማ)፣ ናርዶስ ጌትነት (አዳማ ከተማ)፣ ታሪኳ ደቢሶ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ብዙዓየሁ ታደሰ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ማህደር ባዬ (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ፍሬወይኒ ገብረፃድቅ (ኤሌክትሪክ)

አማካዮች
እመቤት አዲሱ (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ የምስራች ላቀው (አዳማ ከተማ)፣ ገነት ኃይሉ (አዳማ ከተማ)፣ ዙፋን ደፈርሻ (ሀዋሳ ከተማ)፣ እፀገነት ግርማ (ጌዴኦ ዲላ)፣ አረጋሽ ካልሳ (መከላከያ)፣ ሲሳይ ገብረዋህድ (መከላከያ)፣ ማህሌት ታደሰ (አቃቂ ቃሊቲ)፣ ብርቄ አማረ (አቃቂ ቃሊቲ)

አጥቂዎች
ሳራ ነብሶ (አዳማ ከተማ)፣ ነፃነት መና (ሀዋሳ ከተማ)፣ ሥራ ይርዳው (ድሬዳዋ ከተማ)፣ ረድኤት አስረሳኸኝ (ጌዴኦ ዲላ)፣ አይዳ ዑስማን (መከላከያ)፣ ዮርዳኖስ ምዑዝ (መቐለ 70 እንደርታ)


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ