ወልዋሎ ስታዲየሙ እንዲገመገምለት በደብዳቤ ጠየቀ

ወልዋሎዎች ላለፉት ሁለት ዓመታት ገደማ በዕድሳት ላይ የቆየውና በቅርቡ የሚጠናቀቀው ስታዲየማቸው በአወዳዳሪው አካል እንዲገመገምላቸው በደብዳቤ ጠየቁ።

ቢጫ ለባሾቹ ከፍ ያለ የጥራት ደረጃ ያለው የመጫወቻ ሜዳ እንደሰሩ የተነገረ ሲሆን የመልበሻ ክፍልን ጨምሮ የአጥር እና ተያያዥ ሥራዎች በመስራት ላይ ይገኛሉ። በዐቢይ ኮሚቴው ፍቃድ የሚያገኙ ከሆነም ከሁለተኛው ዙር ጀምሮ በስታዲሙ መጫወት ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሣር ሥራዎች፣ የግብ ብረት እና የመስመር ሥራዎች የተጠናቀቀለት ይህ ስቴድየም የቀረው የአጥር ሥራዎች በክለቡ በጎ ፍቃድ ደጋፊዎች መሰራት ጀምሯል።

ክለቡ ለዐቢይ ኮሚቴ የላከው ደብዳቤ 👇


© ሶከር ኢትዮጵያ