ፌዴሬሽኑ በወልዋሎ እና የቀድሞ ተጫዋቾቹ ዙርያ ውሳኔ አሳልፏል

ባለፈው የውድድር ዘመን በወልዋሎ ሲጫወቱ የነበሩ እና ወርሀዊ ደመወዛችን አልተከፈለንም በማለት ቅሬታን ያሰሙ ስምንት ተጫዋቾችን አስመልክቶ ፌዴሬሽኑ ውሳኔን ሰጥቷል፡፡

በ2011 የውድድር ዘመን በወልዋሎ ውስጥ ሲጫወቱ የነበሩት ኤፍሬም አሻሞ፣ አማኑኤል ጎበና፣ ብርሀኑ አሻሞ፣ ብርሀኑ ቦጋለ፣ ዳንኤል አድሓኖም፣ ቢኒያም ሲራጅ፣ ደስታ ደሙ እና ሳምሶን ተካ “የሰኔ ወር ደመወዝ በተደጋጋሚ እንዲከፈለን ብንጠይቅም ክለቡ ተግባራዊ ሊያደርግልን አልቻለም።” በማለት ለሁለት ጊዜያት ለፌዴሬሽኑ የቅሬታ ደብዳቤን ያስገቡ ሲሆን የፌዴሬሽኑ የዲሲፕሊን ኮሚቴም የመጨረሻ ያለውን ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚህም መሠረት ክለቡ ለስምንቱም ተጫዋቾች በሰባት ቀናት ውስጥ ተገቢውን ክፍያ እንዲፈፅም ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ ይህን ውሳኔ በተያዘው የቀን ገደብ ተግባራዊ ካላደረገ ከፌዴሬሽኑ ምንም አይነት አገልግሎት እንደማያገኝም ኮሚቴው ጨምሮ ገልጿል፡፡

የውሳኔው ደብዳቤ👇

© ሶከር ኢትዮጵያ