ሙሉዓለም መስፍን ለትውልድ ከተማው ክለብ የትጥቅ ድጋፍ አደረገ

የቅዱስ ጊዮርጊሱ የተከላካይ አማካይ ስፍራ ተጫዋች ሙሉዓለም መስፍን የትውልድ ከተማው ክለብ ለሆነው ጋሞ ጨንቻ የትጥቅ ድጋፍን አድርጓል፡፡

ሙሉዓለም ከሦስት ዓመት በፊት የተቋቋመውና ዘንድሮ ወደ ከፍተኛ ሊግ በማደግ እየተሳተፈ ያለው ጋሞ ጨንቻ በጨዋታ ጊዜ የሚጠቀምበትን መለያ እና የመመገቢያ ትጥቅን ነው በስጦታ መልክ ያበረከተው፡፡

ተጫዋቹ ስጦታውን አስመልክቶ ለሶከር ኢትዮጵያ በሰጠው አስተያየት “እኔ በዛ ከተማ እያለው አንድም ክለብ አልነበረም። ይህ ክለብ አሁን በቅርቡ ነው የተቋቋመው። ተወልጄም ተምሬም ያደግኩበት በመሆኑ ድጋፌ በዚህ ብቻ አያቆምም። ይህን ያደረኩት ለጊዜው ነው፡፡ ከደቡብ አፍሪካ የተሻሉ መለያዎች፣ ኳሶች እና የተለያዩ የልምምድ ቁሳቁሶችን ለማስመጣት እየተንቀሳቀስኩ ነው። በቀጣይ ከዚህ በተሻለ መልኩ ለቡድኑ አበረክታለሁ።” ሲል ተናግሯል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ