የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ታውቋል

ለአንድ ወር ያህል ተቋርጦ የቆየው የሴቶች ፕሪምየር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ታውቋል።

ሁለቱም የሴቶች ታዳጊ ብሔራዊ ቡድኖች ባደረጓቸው የማጣርያ ጨዋታዎች ምክንያት ከአራተኛው ሳምንት ፍፃሜ በኋላ ተቋርጦ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን የ17 ዓመት በታች ቡድኑ ከማጣርያው በመውጣቱ እና የ20 ዓመት በታች ቡድኑ ደግሞ በዚህ ሳምንት የመጀመርያ ዙር የመልስ ጨዋታውን የሚያከናውን በመሆኑ የ5ኛ ሳምንት መርሐ ግብር የሚቀጥል ይሆናል። በዚህም መሠረት ከጥር 26 እስከ 28 ባሉት ቀናት የ5ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

የሴቶች ፕሪምየር ሊግን ከአራት ሳምንታት ጨዋታዎች በኋላ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአስር ነጥብ ሲመራ አዳማ ከተማ በስምንት ነጥብ ይከተላል። አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ በአራቱ ሳምንታት ነጥብ ያላስመዘገበ ቡድን ነው።

ፕሪምየር ሊጉ በተጠቀሱት ሦስት ቀናት እንደሚደረግ ቢጠቀስም ጨዋታዎቹ የሚደረጉበት የተናጠል ቀን እስካሁን ድረስ አልታወቀም። ቀኖቹ ሲታወቁም እየተከታተልን የምናቀርብ ይሆናል።

የ5ኛ ሳምንት ጨዋታዎች

👉 አዳማ ከተማ ከ መከላከያ
👉 አቃቂ ቃሊቲ ከ መቐለ 70 እንደርታ
👉 ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ አዲስ አበባ ከተማ
👉 ድሬዳዋ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ
👉 ሀዋሳ ከተማ ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

© ሶከር ኢትዮጵያ