አዳማ ከተማ አዲስ ፕሬዝዳንት ሾሟል

አዳማ ከተማ በክለቡ ውስጥ የተፈጠረውን አለመረጋጋት የመቅረፍ ትልቅ የቤት ሥራ የሚጠብቃቸው አዲስ ፕሬዝዳንት ሾሟል።

ደጋፊዎች ከሜዳ እየሸሹበት የመጣውና የክለቡን መሠረት እያናጋው የሚገኘውን የፋይናስ እጥረት የመቅረፍ ትልቅ የቤት ሥራ የሚጠብቃቸው አቶ ገመቹ መኮንን በጤና እክል ምክንያት በመደበኛ ሥራቸው የማይገኙት አቶ ተስፋዬን በመተካት ነው ፕሬዝዳንት በመሆን የተሾሙት። የክለቡን ባህል እና አሰራር ጠንቅቀው እንደሚያውቁ የሚነገርላቸው አቶ ገመቹ ክለቡ ያጋጠመውን ችግር በቀጣይ ያስተካክሉታል ተብሎ ተስፋ ተጥሎባቸዋል።

በሌላ ዜና ይህን ዘገባ እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ቡድኑ አሁን ልምምዱን በበቂ ሁኔታ እየሰራ ቢገኝም የተጫዋቾቹ ጥያቄ እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ ሰምተናል።

አዳማ ከተማ በ12ኛው ሳምንት በመጪው እሁድ በሜዳው ኢትዮጵያ ቡናን ያስተናግዳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ