የአሰልጣኞች አስተያየት | ጅማ አባ ጅፋር 1-0 መቐለ 70 እንደርታ

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት ጅማ መቐለን ከረታበት ጨዋታ በኋላ የጅማው አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው አስተያየት ሲሰጡ የመቐለው ገብረመድህን ኃይሌ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

” ያስቆጠርነውን ጎል ማስጠበቅ ነበረብን ፤ ተሳክቶልናል ” ጳውሎስ ጌታቸው (ጅማ አባ ጅፋር)

ስለጨዋታው

ጥሩ ጨዋታ ነበር ፤ በሁለታችንም በከል ጥሩ የኳስ ፍሰት ነበር። መጨረሻ ደቂቃዎች ላይ እነሱ አጥቅተው ተጫውተዋል። እኛ ደግሞ ያስቆጠርነውን ጎል ማስጠበቅ ነበረብን ፤ ተሳክቶልናል።

ቡድኑ በሁለተኛው አጋማሽ ስለሚታይበት መዳከም

መዳከም ሳይሆን፤ ቀድመን አግብተን እሱን ለማስጠበቅ ነው። ካለንበት ደረጃ አንፃርም ተጫዋቾቹም ልምድ የሌላቸው ከመሆኑ አንፃር ነው።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ