በአራት የ13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ላይ የቀን ለውጦች ተደርገዋል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 13ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከቅዳሜ ጀምረው ሲከናወኑ የመርሐ ግብሩ አካል የሆኑ አራት ጨዋታዎች የቀን ለውጥ ተደርጎባቸዋል። 

ለውጥ ከተደረገባቸው ጨዋታዎች መካከል የሀዲያ ሆሳዕና እና ወላይታ ድቻ ጨዋታ አንዱ ነው። ጨዋታው እሁድ አቢዮ ኤርሳሞ ላይ እንዲከናወን ቢወሰንም ሀዲያ ሆሳዕና ሁለት የሜዳው ጨዋታዎችን በገለልተኛ ሜዳ እንዲያደርግ በመቀጣቱ ምክንያት ወደ ሀዋሳ ተዘዋውሯል። በዚህም ማክሰኞ የካቲት 3 የሚከናወን ይሆናል። 

በሀዋሳ ቅዳሜ እና እሁድ ሊደረጉ የነበሩት ሁለት ጨዋታዎች በአንድ ቀን ተገፍተው እሁድ እና ሰኞ ይከናወናሉ። ቅዳሜ የነበረው የሀዋሳ ከተማ እና ጅማ አባ ጅፋር ጨዋታ እሁድ ሲወናወን እሁድ የነበረው የሲዳማ ቡና እና አዳማ ከተማ ጨዋታ ወደ ሰኞ ተሸጋሽጓል። የእነዚህ ጨዋታዎች የቀን መሸጋሸግ ምክንያት ግን አልታወቀም። 

ሌላው በዚህ ሳምንት የቀን ሽግሽግ የተደረገበት ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና እና ወልቂጤ ከተማ ጨዋታ ነው። እሁድ ሊደረግ የነበረው ይህ መርሐ ግብር በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ምክንያት ወደ ሐሙስ የካቲት 5 (10:00) ሊሸጋገር ችሏል። 

የተሻሻለው የ13ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይህንን ይመስላል


13ኛ ሳምንት
ቅዳሜ ጥር 30 ቀን 2012
መቐለ 70 እንደርታ 9:00 ፋሲል ከነማ
እሁድ የካቲት 1 ቀን 2012
ሀዋሳ ከተማ 9:00 ጅማ አባ ጅፋር
ባህር ዳር ከተማ 9:00 ሰበታ ከተማ
ድሬዳዋ ከተማ 9:00 ስሑል ሽረ
ወልዋሎ ዓ/ዩ 9:00 ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰኞ የካቲት 2 ቀን 2012
ሲዳማ ቡና 9:00 አዳማ ከተማ
ማክሰኞ የካቲት 3 ቀን 2012
ሀዲያ ሆሳዕና 9:00 ወላይታ ድቻ
ሐሙስ የካቲት 5 ቀን 2012
ኢትዮጵያ ቡና 10:00 ወልቂጤ ከተማ

©ሶከር ኢትዮጵያ