የሀዋሳ ረዳት አሰልጣኝ ከክለቡ ጋር ይገኛሉ

በትናንት ዘገባችን ከክለቡ መሰናበታቸውን ገልፀን የነበረው የክለቡ ረዳት አሰልጣኝ አምጣቸው ኃይሌ አሁንም ከክለቡ ጋር ይገኛሉ፡፡

በትናንቱ ዘገባችን ረዳት አሰልጣኙ አምጣቸው ኃይሌ መሰናበታቸውን የሚገልፀው ዜና በመረጃ ክፍተት የተሰራ መሆኑን እየገለፅን አሰልጣኙ በስራቸው ላይ እንዳሉ ከክለቡ የበላይ አካላት ያረጋገጥን ሲሆን ለተፈጠረው ስህተትም ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

ከክለቡ ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም የሀዋሳ ከተማ ደጋፊዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት በመሆን ክለቡን ሲያገለግሉ ቆይተው በቡድን መሪነት ደግሞ ከ2011 መስከረም ወር አንስቶ ሲመሩ የነበሩት አቶ ደሬሳ ዱካሞ ለክለቡ የመልቀቂያ ደብዳቤ ስለማስገባታቸው ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር ባደረጉት ቆይታ አረጋግጠዋል፡፡ ሀዋሳ ከተማ ፋሲል ከተማን 3-2 ሲያሸንፍ ቡድን መሪው በገዛ ፍቃዳቸው በመልቀቃቸው በጊዜዊው ቡድን መሪ ቅዱስ ዘሪሁን መሪነት ጨዋታውን ማካሄዳቸው ይታወሳል፡፡

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ