አዳማ ከተማ የፊታችን ሐሙስ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ያደርጋል

አዳማ ከተማ በቢራ ምርቶቹ ከሚታወቀው ዩናይትድ ቢቨሬጅስ ጋር ይፋዊ የውል ስምምነት ሐሙስ ያደርጋል።

የመጠጦች አምራች ኩባንያው አንበሳ ቢራን ለገበያ በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን የፊታችን ሀሙስ በአዳማ ሮቢ ሆቴል የሚድያ አካላት በተገኙበት ከአዳማ ከተማ ክለብ ጋር የአምስት ዓመት የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት የሚፈፅም ይሆናል። የስፖንሰር ሺፑ ዋና አላማ ቡድኑን እና የኢትዮጵያ ስፖርትን መርዳት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን በውስጡ ያካተታቸው ጉዳዮች ሀሙስ በሚኖረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይገለፃል ተብሏል።

© ሶከር ኢትዮጵያ