ሀዲያ ሆሳዕና አይቮሪኮስታዊውን አጥቂ አስፈረመ

አሰልጣኝ ፀጋዬ ኪዳነማርያም የሁለተኛው ዙር ፈራሚ ተጫዋች በማድረግ አይቮሪኮስታዊው የስሑል ሽረ አጥቂ ሳሊፍ ፎፋናን አስፈርመዋል፡፡

ዐምና በዚህ ወቅት ስሑል ሽረን ተቀላቅሎ የነበረው እና ክለቡ በሊጉ እንዲቆይ ከረዱ ተጫዋቾች መካከል ግንባር ቀደሙ የነበረው ሳሊፍ ፎፋና ከቀናት በፊት ውሉ በመጠናቀቁ ወደ ተለያዩ ክለቦች ያመራል ቢባልም ማረፊያው ሀዲያ ሆሳዕና መሆኑን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡ ለቀጣዩ 1 ዓመትም በነብሮቹ ቤት ቆይታ ይኖረዋል።

በ2011 በፕሪምየር ሊጉ የግማሽ ዓመት ቆይታው 11 ጎሎችን አስቆጥሮ የነበረው የቀድሞው አል አልሙራ፣ አፍሪካን ስፖርትስ እና ማንጋ አጥቂ ዘንድሮ 2 ጎሎች ብቻ በማስቆጠር ቢቀዛቀዝም በቅርብ ሳምንታት ወደ ጥሩ አቋሙ እየመለሰ እንደመሆኑ ሁለት አጥቂዎችን አሰናብቶ የአጥቂ ተጫዋች እጥረት ለገጠመው ሆሳዕና የፊት መስመር ጥሩ አማራጭ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ