ድሬዳዋ ከተማ ሁለት ተጫዋቾቹ ከጉዳት ተመልሰውለታል

ለሁለተኛው ዙር ልምምዱን ዛሬ የጀመረው ድሬዳዋ ከተማ ረመዳን ናስር እና ሳሙኤል ዘሪሁንን ከጉዳት መመለሳቸውን ክለቡ አስታውቋል።

በቅድመ ዝግጅት ወቅት የባት ጉዳት አጋጥሞት የአንደኛው ዙር ሙሉ ለሙሉ ያመለጠው ረመዳን ናስር ከጉዳቱ ሙሉ ለሙሉ አገግሞ ወደ ልምምድ የተመለሰ ሲሆን ለሁለተኛው ዙር የቡድኑን ማጥቃት ያሰፋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከቡድኑ ተስፈኛ ተጫዋቾች አንዱ የሆነው የአጥቂ ሥፍራ ተጫዋቹ ሳሙኤል ዘሪሁን ቡድኑ ኢትዮጵያ ቡናን አስተናግዶ ያለ ጎል አቻ በተለያየበት ጨዋታ ላይ የብሽሽት ጉዳት ካስተናገደ በኋላ ያለፉትን ሁለት ወራት ከሜዳ ርቆ የቆየ ሲሆን እንደ ረመዳን ሁሉ ከጉዳቱ አገግሞ ለሁለተኛው ዙር ብቁ መሆኑ ተገልጿል።

ድሬዳዋ ከተማ ሁለተኛውን ዙር ሀዋሳ ከተማ እና ፋሲል ከነማን በተከታታይ በሜዳው በማስተናገድ ይጀምራል።

© ሶከር ኢትዮጵያ