ወልቂጤ ከተማ የመጀመሪያ ተጫዋቹን አስፈረመ

ወልቂጤ ከተማ የሙከራ ዕድል ሰቶት የነበረው ጋናዊውን የአማካይ ስፍራ ተጫዋች አልሀሰን ኑሁን የግሉ አድርጓል፡፡

ለጋናዎቹ ሪል ስፖርቲቭ፣ አሻንቲ ጎልድ እና ከ2017 ጀምሮ ደግሞ ለኢዱቢያስ ዩናይትድ በመጫወት ላይ የነበረው ይህ ተጫዋች በ2011 በጥር የዝውውር መስኮት ሲዳማ ቡናን ለመቀላቀል ወደ ኢትዮጵያ ከመጣ በኋላ ከወረቀት ጉዳዮች በጊዜ ያለ መጠናቀቅ ጋር በተያያዘ ለክለቡ ለመፈረም ሳይችል የቀረ ሲሆን ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ዳግም ተመልሶ ሠራተኞቹን በአንድ ዓመት የውል ጊዜ ተቀላቅሏል፡፡ በርካታ የአማካይ ተጫዋቾች በያዘው ወልቂጤም ለተሰላፊነት ፉክክር ይጠብቀዋል።

ይህ ተጫዋች በቅርቡ ድሬዳዋ ከተማን የተቀላቀለው አጥቂው ፉይሴኒ ኑሁ ታናሽ ወንድም ሲሆን በሁለተኛው ዙር ከኦቮኖ ወንድማማቾች በመቀጠል በሊጉ የተጫወቱ ወንድማማች የውጪ ዜጎች እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

©ሶከር ኢትዮጵያ