ፕሪምየር ሊጉ ከሁለት ሳምንት ጨዋታዎች በኋላ ለ21 ቀናት ይቋረጣል

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የሁለት ሳምንታት ጨዋታዎች ከተደረጉበት በኋላ ለ21 ቀናት ይቋረጣል።

ሊጉ ከእረፍት መልስ በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ በሚካሄዱ የ16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሚቀጥል ሲሆን ሐሙስ እና ዓርብ (መጋቢት 3 እና 4) ደግሞ የ17ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከተከናወኑ በኋላ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ዝግጅት እና ጨዋታዎች ለ3 ሳምንታት የሚቋረጥ ይሆናል።

ብሔራዊ ቡድኑ በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ሦስተኛ እና አራተኛ የምድብ ጨዋታውን ከኒጀር ብሔራዊ ቡድን ጋር መጋቢት 19 ከሜዳው ውጪ እንዲሁም ከሦስት ቀናት በኋላ መጋቢት 22 በሜዳው የሚያከናውን ሲሆን ከማጣርያዎቹ ቀደም ብሎ የወዳጅነት ጨዋታ እና ዝግጅት ለማድረግ እንዲረዳ ለ15 ቀናት ዝግጅት ያከናውናል።

ከብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታዎች በኋላ ዓርብ መጋቢት 25 እና ቅዳሜ መጋቢት 26 በሚደረጉ የ18ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ፕሪምየር ሊጉ ከቆመበት የሚቀጥል ይሆናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ