መቐለ 70 እንደርታ ከአማካዩ ጋር ተለያይቷል

ሳሙኤል ሳሊሶ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።

ባለፈው የውድድር ዓመት መከላከያን ለቆ መቐለ 70 እንደርታ በመቀላቀል በመጀመርያዎቹ ሳምንታት ከቡድኑ ጋር ጥሩ አጀማመር የነበረው ፈጣኑ አማካይ በተለይም በመጀመርያው ዙር የቡድኑ ወሳኝ ተጫዋች እስከመሆን ደርሶ ነበር። ክለቡ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ እንዲያነሳ ጥሩ ድርሻ የነበረው ተጫዋቹ በዘንድሮ የመቐለ ቆይታው በተለያዩ ምክንያቶች ቡድኑን ማገልገል ያልቻለ ሲሆን ቀሪ የስድስት ወራት ኮንትራት ቢኖረውም ቋሚ ተሰላፊነትን ፍለጋ ከክለቡ ጋር እንደተለያየ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም በሼር ኢትዮጵያ፣ መከላከያ እና መቐለ 70 እንደርታ መጫወት የቻለው ሳሙኤል ሳሊሶ በቀጣይ ቀናት ወደ አንድ የፕሪምየር ሊግ ቡድን ያመራል ተብሎ ይጠበቃል።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ