ሲዳማ ቡና ከአጥቂ ተጫዋቹ ጋር ተለያየ

በዓመቱ መጀመርያ ሲዳማን ተቀላቅሎ የነበረው አጥቂው ሙሉቀን ታሪኩ ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

የቀድሞው የባህርዳር ከተማ ተጫዋች በ2011 የጣና ሞገዶቹን ከለቀቀ በኋላ ወደ ቀድሞ ክለቡ አዳማ ከተማ ቢመለስም የአንድ ዓመት ውል እየቀረው ከስድስት ወራት በፊት ወደ ሲዳማ ቡና ማምራቱ ይታወሳል፡፡ ለአንድ ዓመት ያህል በክለቡ ቆይታን ለማድረግ ፈርሞ የነበረው አጥቂው በመጀመርያ አሰላለፍ ለመግባት በመቸገሩ የስድስት ወራት ውል እየቀረው ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡

ከክለቡ ጋር በተያያዘ ለሁለተኛው ዙር ራሱን አጠናክሮ ለመቅረብ ለሁለት የአጥቂ እና የተከላካይ የውጪ ዜጋ ተጫዋቾች የሙከራ ዕድልን እየሰጠ ይገኛል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ