ወልቂጤ ከተማ ኮሮና ቫይረስን ለመግታት የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል

የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ለኮሮና መከላከል የሚውል ለቁሳቁስ መግዣ ግማሽ ሚልዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ክለቡ በጉራጌ ዞን አካባቢ ስርጭቱን ለመከላከል ለሚደረጉ ተግባራት እና ለአቅመ ደካሞች የንፁህና መጠበቂያ ግዢ የሚውል ከተጫዋቾች እና ከአሰልጣኝ ቡድን አባላት ከደመወዛቸው 20% በድምሩ 286,400 (ሁለት መቶ ሰማንያ ስድስት ሺህ አራት መቶ ብር) እንዲሁም የክለቡ ፅህፈት ቤት ሰራተኞች 50% በድምሩ 21,663 (ሀያ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ስልሳ ሶስት ብር)፣ ክለቡ ደግሞ መንግስት ከበጀተለት 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በአጠቃላይ በድምሩ 508,063 (አምስት መቶ ስምንት ሺህ ስልሳ ሦስት ብር) የገንዘብ ድጋፍ ለዞኑ አድርጓል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ