የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውል ድጋፍ አድርጓል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአደገኛ ሁኔታ እየተዛመተ የሚገኘው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል ድጋፍ ማድረጉን በድረገፁ አስታውቋል።

ፌዴሬሽኑ በድረ-ገፁ እንዳስታወቀው “የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በስልክ ከፕሬዝዳንት ኢሳይያስ ጂራ ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ፌዴሬሽኑ የፋይናንስ እጥረት እንዳለበት ቢታወቅም ከዚህ ጉዳይ የሚብስ ነገር የለም በማለት የ500,000 ( የአምስት መቶ ሺህ ብር) ድጋፍ አድርጓል።” ብሏል። ይህንን ገንዘብ በብሔራዊ ደረጃ የተቋቋመው ኮሚቴ ባዘጋጀው የባንክ ሒሳብ ገቢ የተደረገ ሲሆን ፕሬዝዳንቱም ክለቦች የተጀመረውን ተግባር በመደገፍ የበኩላቸውን እንዲወጡ አደራ ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ አያይዘው እንደገለፁት በየአካባቢው የሚደረጉ የማስ ስፖርት እንቅስቃሴዎች ለበሽታው ተጋላጭነታችንን ሊጨምሩ ስለሚችሉ ብሎም ለቫይረሱ መስፋፋት ምቹ ሁኔታን ስለሚፈጥሩ መንግስት በሰጠው መመርያ መሰረት በጋራ ከሚሰሩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ማኅበረሰቡ እዲቆጠብ አሳስበዋል።

© ሶከር ኢትዮጵያ