ሳላዲን ሰዒድ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል

የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ማኅበር ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል በሀገር ደረጃ ለሚደረገው ጥረት የራሱን ድርሻ እየተወጣ የሚገኘው የኢትዮጵያ ተጫዋችች ማኀበር የተለያዩ ቁሳቁሶችን የማሰባሰቡን ሒደት ከጀመረ ሰነባብቷል። አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድም ለዚህ በጎ ተግባር ይረዳ ዘንድ በትናትናው ዕለት ማኀበሩ ለዚህ ዓላማ እንዲውል በከፈተው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት 50 ሺህ ብር መለገሱን ለሶከር ኢትዮጵያ አሳውቋል።

በቅርቡ የገንዘብም ሆኖ የቁሳቁስ ማሰባሰቡ ሂደት እንደሚጠናቀቅ ከማኀበሩ የሰማን ሲሆን በቀሪዎቹ ቀናት ይህን በጎ ተግባር ለማገዝ የሚፈልጉ ሌሎች አባላት እና የስፖርት ቤተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርግ ማኀበሩ ጥሪውን አቅርቧል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ